icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ፈጣኑ የፎርትናይት ብሊትዝ ሮያል ሞድ ላይ ማሸነፍ የሚችሉባቸው 5 ቁልፍ ምስጢሮች 

ብሊትዝ ሮያል፣ ፎርትናይት ላይ የሚገኝ ፈጣን የጌም ሞድ ዓይነት ነው። አውሎ ነፋሳት በአስፈሪ ፍጥነት የሚነፍሱበት፣ ውድድሮች በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቁበት እና ምንም ዓይነት ስህተቶች ተቀባይነት የማያገኙቡት ልዩ ሞድ ነው። እዚህ ሞድ ላይ አይበገሬ እና አሸናፊ መሆን ከፈለጉ፣ ወደ ትክክለኛው ቦታ ነው የመጡት! ከዚህ ቀጥሎ አይበገሬ መሆን የሚያስችሉዎትን 5 ቁልፍ ጉዳዮች በዝርዝር አዘጋጅተናል። 

የመጀመሪያው፣ የሚያርፉበትን ቦታ በጥንቃቄ ይምረጡ። ሁሉም ለማረፍ የሚመርጣቸውን ትላልቅ ከተሞች ይርሷቸው፣ ገና እንዳረፉ ሽጉጥ በመተኳኮስ ብቻ የመጀመሪያዎቹን ሁለት ደቂቃዎች ማባከን ብቻ ነው ትርፉ፤ ይልቅ ዋና ከሚባሉ አካባቢዎች ትንሽ ራቅ ብሎ የሚገኝ ቦታ ላይ ይረፉ እና በፍጥነት ወሳኝ መሳሪያዎችን እና የፈውስ ግብዓቶችን ብቻ በመሰብሰብ ጉዞዎን ይቀጥሉ። ብሊትዝ ላይ ዘና ብለው መዘዋወር የሚያስችሉዎ በቂ ጊዜ የለዎትም። ቀጥታ ወደ ስራ! 

በሁለተኛ ደረጃ፣ አይፍዘዙ፣ በንቃት ይጫወቱ። ካምፕ ማድረግን አያስቡት፤ አፍታ ሳይቆዩ አውሎ ነፋስ ጠራርጎ ነው የሚወስድዎት። ትጥቅቆችዎን ማሻሻል እንዲችሉ አካባቢዎ ላይ የሚገኙ ጠላቶች ጋር ቀላል እና ፈጣን ውጊያዎችን ያድርጉ፤ ነገር ግን በፍጹም ጠላቶችን ረጅም ርቀት ለማሳደድ እንዳይሞክሩ፤ መጨረሻዎ የአውሎ ነፋስ እራት መሆን ነው። እንዲሁም የሌሎች ተጫዋቾችን ትኩረት በመሳብ ትጥቆቻቸውን መዝረፍ እንዲችሉ የተኩስ ድምፆችን ይጠቀሙ። 

ሶስተኛው ወሳኝ ጉዳዮች ግብዓቶች ናቸው። መደበኛ ጨዋታ ላይ እንደለመዱት ግብዓቶችን ቀስ ብለው ማከማቸት የሚችሉበት ጊዜ የለዎትም፤ ስለዚህ ወሳኝ ሰዓቶች ላይ እንዲያገለግሉዎ፣ መንገድዎ ላይ የሚያገኟቸውን ግብዓቶች እየሰበሰቡ ይለፉ። መጨረሻ ላይ በአግባቡ የተቀመጠ አንድ ግድግዳ አሸናፊነትዎን ወይም ወደ ሎቢ ተመላሽነትዎን ሊወስን ይችላል። 

አራተኛው፣ መንቀሳቀስዎን በፍጹም እንዳያቆሙ። እንደ ዚፕ-ላይኖች፣ ተሽከርካሪዎች፣ መንቀሳቀሻ መሳሪያዎች ያሉ ካርታውን በፍጥነት ለመሻገር የሚረዱዎትን ዘዴዎች ሁሉ ጥቅም ላይ ያውሉ። አንድ ቦታ ላይ ለረጅም ጊዜ ከቆዩ፣ ወይ ተተኩሶብዎት ይሞታሉ ወይም አውሎ ነፋሱ ጠራርጎ ይወስድዎታል። ብሊትዝ ላይ መንቀሳቀስ ህልውናዎን የሚወስን ቁልፍ ጉዳይ ነው። 

አምስተኛ እና የመጨረሻው፤ ለፍጻሜው ዝግጁ ይሁኑ። ጨዋታው ፈጣን ስለሆነ፣ መጨረሻው ዙር ላይ በርካታ ተጫዋቾች ስለሚቀሩ በጥንቃቄ ሊወጡት ይገባል። ከቻሉ ከፍ ያለ ቦታ ላይ በማድፈጥ፣ ሌሎቹ እርስ በራሳቸው እስኪጨራረሱ ይጠብቁ እና ሁለት ወይም ሦስት ተጫዋቾች ብቻ መቅረታቸውን እንዳወቁ፣ ጦርነቱን በመቀላቀል በቀላሉ አሸናፊነትን መቀዳጀት ይችላሉ። 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !