
አዲሱ የፎርትናይት ሲዝን ላይ በርካታ አስገራሚ አዳዲስ ነገሮች ተጨምረዋል፣ ሆኖም ግን አሁንም ሊጠቀሟቸው የሚችሉ ጥቂት የቆዩ ወሳኝ መሳሪያዎች አሁንም ይገኛሉ። ቅድሚያ የሚሰጧቸው ወይም የሚጠቀሟቸው የመሳሪያ እና የግብዓት አይነቶች ከሚጠብቁት በላይ አጨዋወትዎ ላይ ታላቅ ልዩነት ሊፈጥሩ ይችላሉ። አይበገሬ እና ሁሌ አሸናፊ መሆን ከፈለጉ ቀጥለን ያስቀመጥናቸውን ምርጥ 5 ምርጫዎች አሁኑኑ መጠቀም ይጀምሩ።
አንደኛ ላይ የሚገኘው፣ አንጋፋውን Shotgun ነው። እያንዳንዱ ሲዝን ላይ አንድ የልብ አድርስ የሆነ Shotgun መኖሩ የማይቀር ነው፣ አሁንም ቢሆን ለቅርብ ርቀት ውጊያዎች የግድ ሊጠቀሙት የሚገባ መሳሪያ ነው። ጠላት ላይ ከባድ ጉዳት ለማድረስ ይሁን፣ በፈጣን ተኩሶች ለማስጨነቅ፣ ይህ መሳሪያ ለማንኛውም የቅርብ ርቀት ውጊያዎች የሚሆን ወሳኝ መሳሪያ ነው። እንዲሁም ከከባድ ግብዓቶች ጋር በማጣመር አስጨናቂ የቅርብ ርቀት ውጊያዎች ላይ አይበገሬ መሆን ያስችልዎታል።
ቀጣዩ፣ Assault Rifle ሲሆን አሁንም ወደር የማይገኝነት አስተማማኝ አማራጭ ነው። የመካከለኛ ርቀት ውጊያዎች ላይ ጫና ለመፍጠር እና የጠላት ግንባታዎችን ማፍረስ የሚያስችል ምርጥ ጠመንጃ ነው። የአሁኑ ሲዝን ላይ፣ አንዳንድ የAR አማራጮች በጣም አስተማማኝ ከመሆናቸው የተነሳ ጥቃት የሚያደርሱበት ተጫዋች ምንም ሳያውቅ ዒላማ ውስጥ እንዲያስገቡት (laser) ያስችሉዎታል። ዋናው ነገር ጠላትዎ ማምለጥ በሚሞክርበት ወቅት ተኩስዎ እንዳይቋረጥ ሁልጊዜ በቂ ጥይት መያዝዎን ያረጋግጡ።
ሶስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙት ስናይፐሮች እና precision መሳሪያዎች ናቸው። መንቀሳቀስ ወሳኝ ጉዳይ በሆነበት በዚህ ጌም፣ በአግባቡ የተተኮሰች አንድ ጥይት የጨዋታውን ሂደት ወዲያውኑ የመቀየር አቅም አላት። አንድም ጥይት ትሁን ያልተዘጋጀ እና ለአደጋ ራሱን ያጋለጠ ተጫዋች ላይ መተኮስን የመሰለ አሁንም እጅግ የሚያረካ ነገር የለም። የሚጠበቅብዎ ከፍታ ያለው ቦታ ላይ ስናይፐርዎን ዝግጁ በማድረግ ካምፐሮችን ወይም ዝም ብለው የሚንቀዋለሉ ተጫዋቾችን መቀጣጫ ማድረግ ነው።
በአራተኛ ደረጃ፣ በጣም አስፈላጊ የምንላቸው የእንቅስቃሴ ግብዓቶች ናቸው። መሳሪያ እኮ አይደሉም? ሊሉ ይችላሉ፣ አዎ፣ መሳሪያዎች አይደሉም፣ ነገር ግን አሁን ባለው የፎርትናይት ሁኔታ በፍጥነት መንቀሳቀስ መቻል ተጨማሪ መሳሪያዎችን ከመያዝ የበለጠ ዋጋ አለው። Shockwaves፣ Grapplers፣ Vehicles ... ጠላትን ለመግፋትም ይሁን ለማምለጥ ሁሌም ቢሆን በፍጥነት ቦታ መቀየር የሚችሉበት መንገድ ሊኖርዎ ይገባል። በህይወት የሚቆየው፣ መንቀሳቀስ የሚችል ተጫዋች ብቻ ነው።
በመጨረሻም፣ ቢያንስ አንድ የፈውስ ግብዓት ትጥቅዎ መኃል መኖሩን ያረጋግጡ። Mini-shields አሁንም ቢሆን ቁጥር አንድ አማራጮች ናቸው፤ ሆኖም ግን በዚህ ሲዝን የተካተቱ አንዳንድ የማገገሚያ ግብዓቶች በጣም ወሳኝ ከመሆናቸው የተነሳ ምንም ተስፋ የለውም የተባለ ተጫዋችን ድል ሊያቀዳጁ ይችላሉ። በኃላ ፀፀት ውስጥ ከሚገቡ እነዚህን ግብዓቶች ሳይዙ በፍጹም የትም አይንቀሳቀሱ።
መልካም ዕድል!