icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ቼዝ ላይ እንዴት የተቀናቃኝዎን ድክመት ማወቅ እና ጥቅም ላይ ማዋል ይቻላል? 

ተቀናቃኝዎ ማንኛውንም እንቅስቃሴዎች ካደረገ በኋላ በቅድሚያ ማድረግ ያለብዎ ነገር ቢኖር፣ የትኛው ቦታ ላይ ክፍተት እንደፈጠረ መመልከት ነው። ለምሳሌ፦ አንድ ወታደሩን ወደፊት ካስጠጋ፣ ከበስተጀርባ የሚገኘው ቦታ ላይ ክፍተት መፍጠሩ የማይቀር ነው። ይህን መሰል ድክመቶችን ልብ ካሉ፣ ወደፊት የተጠጋው ወታደር ዒላማዎ መሆኑ ወይም ሊንቀሳቀሱበት የሚችሉ ቦታን መክፈቱ የማይቀር ነው። 

በመቀጠል፣ የትኛው የቼዝ ጠጠር ነው ጠባቂ የሌለው? ብለው ራስዎን ይጠይቁ። ብዙውን ጊዜ ጀማሪ ተጫዋቾች አንድ የቼዝ ጠጠርን ካንቀሳቀሱ በኋላ የመከላከያ እቅድ መንደፉን ይዘነጉታል። የተቀናቃኝዎ ፈረስ፣ ጳጳስ ወይም ግንብ ያለጥበቃ መተዋቸውን ካስተዋሉ፣ ተቀናቃኝዎ የመከላከያ እርምጃዎችን በመውሰድ ጊዜውን በከንቱ እንዲያባክን፣ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ ማጥቃት የሚችሉበትን ስልት ሊነድፉ ይገባል። 

እንዲሁም ምንም የጥቃት ወይም የመከላከል ዓላማን የማይከተሉ እንቅስቃሴዎች ላይ ትኩረት ያድርጉ። ተቀናቃኝዎ ያለ ምንም ግልጽ ዓላማ የቼዝ ጠጠሮቹን የሚያንቀሳቅስ ከሆነ ጊዜውን በከንቱ እያባከነ ነው። ስለዚህ ይህን ወሳኝ ጊዜ፣ የራስዎን ቼዞች አቀማመጥ ለማደላደል ወይም ጥቃት ለመሰንዘር ሊጠቀሙበት ይገባል። 

ሌላው በብዛት የሚስተዋለው የተለመደ ስህተት፣ ተቀናቃኝዎ ጨዋታው ከመጀመሩ የንጉሱን ደኅንነት ለአደጋ ሲያጋልጥ ነው። ለምሳሌ፦ ከካስትሊንግ አቋሙ ፊት በርካታ ወታደሮችን ከገፋ ወይም አደገኛ ወደሆኑ ሁኔታዎች ካስት በሚያደርግበት ወቅት መስመሮችዎን መክፈት እና ወሳኝ የቼዝ ጠጠሮችዎን (ንግሥት እና ግንብ) በመጠቀም ተቀናቃኝዎ ላይ ጫና መፍጠር የሚችሉበት ጥሩ አጋጣሚ ነው። 

በመጨረሻም፣ አንድን ስህተት በጥሩ መንገድ መቅጣት ካልቻሉ ፋይዳ ቢስ መሆኑን ያስታውሱ። አደገኛ እርምጃዎችን ለማድረግ ከመወሰንዎ በፊት ጥሩ የቼዞች ጥምረት እንዳለዎ በቅድሚያ ያረጋግጡ። ምን ሰውተው፣ ምን ማግኘት እንደሚችሉ በጥንቃቄ ያስሉ፣ የንጉስዎን ደህንነት ይፈትሹ፣ እንዲሁም አስፈላጊ የቼዝ ጠጠር አለመዘንጋትዎን እርግጠኛ ይሁኑ። 

ብቃትዎን ማሻሻል እንዲችሉ፣ ተፎካካሪዎ እያንዳንዱን እንቅስቃሴዎች ካደረገ በኃላ፣ የሚከተሉትን ሦስት ወሳኝ ጥያቄዎ ራስዎን ይጠይቁ፦  

  • ይህ እንቅስቃሴ ምን ጥቃት ሊያደርስ ወይም ምን ሊከላከል ይችላል? 

  • የትኛው ቦታ ወይም የቼዝ ጠጠር ላይ ክፍተት ተፈጥሯል? 

  • ይህን እድል አሁኑኑ መጠቀም እችላለሁ፣ ወይስ በቅድሚያ አቋሜን ማሻሻል አለብኝ? 

እነዚህን ቁልፍ ጉዳዮች እና ስልቶች ጨዋታዎ ላይ መተግበር ከጀመሩ፣ ሊፈትንዎ እና ሊያሸንፍዎ የሚችል ተቀናቃኝ አይኖርም! 

መልካም እድል! 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !