
2025 ለኒንቴንዶ አስደናቂ ነገሮችን የሰነቀ ይመስላል። በቅርቡ Super Mario Bros Wonder ስዊች 2 ላይ እንደሚለቀቅ ይፋ አድርገዋል። ይህ ቪዲዮ ጌም በመጀመሪያ እ.ኤ.አ. በ2023 የመጀመሪያው ስዊች ላይ ተለቆ የነበረ ሲሆን፣ ክላሲክ 2D ይዘቱ እና በWonder Flower የተሞላው ድንቅ ዓለሙ የበርካታ ተጫዋቾችን ልብ መማረክ ችሎ ነበር። አሁን የሚለቀቀው አዲስ እትም ብቻ አይደለም፤ የSwitch 2ን አቅም ሙሉ በሙሉ የሚጠቀም፣ በዶክ በኩል 4K ምስሎች፣ አነስተኛ የሎዲንግ ቆይታ እና የተሻሻሉ አዲስ የመቆጣጣሪዎች አጠቃቀምን ይዞ የሚቀርብ ነው።
የማሪዮ ዓለም በአስደናቂ ቀለማት ያሸበረቀ፣ የማይቆራረጡ አኒሜሽኖችን ያካተተ ከመቼውም ጊዜ የበለጠ ልዩ እትም ነው! እንዲሁም ከWonder Flower ጋር የተያያዙ ነገሮቹ ማሻሻያ የተደረገላቸው በመሆኑ፣ እያንዳንዱን ደረጃ የበለጠ ሕያው እና አስደናቂ ያደርጉታል።
ይህንንም አስመልክቶ ሰብሳቢዎች ሊያመልጣቸው የማይገባ ልዩ ስብስቦችን ኒንቴንዶ ለቋል። እነሱም፦ የጌሙን ፊዚካል ኮፒ ከልዩ የሽፋን ምስል ጋር፣ የማሪዮ እና የሉዊጂ ገጽታ ያላቸው ጥንድ ጆይ-ኮን፣ የጌሙን እድገት የሚሳዩ አዳዲስ ንድፎች የያዘ የስእል ደብተር፣ የማሪዮ ገጽታ ያለው የዝሆን ምስል፣ እና እንደ ገፀ-ባሕሪያን አልባሳት ያሉ እና ተጨማሪ ይዘቶችን መክፈት የሚያስችሉ ኮዶች ይገኙበታል።
ከሁሉም በላይ ግን ያካተታቸው አዳዲስ ተጨማሪ ይዘቶች ናቸው። ኒንቴንዶ የተለያዩ አዳዲስ ዓለማት ላይ ወደ 20 የሚደርሱ አዳዲስ ደረጃዎችን፣ እስከ አራት የሚሆኑ ተጫዋቾችን የሚያሳትፉ የትብብር ውድድሮች፣ እና ዴዚ እና ሮዛሊና የተባሉ ሁለት አዳዲስ ገፀ-ባሕሪያትን ያካተታል። እንዲሁም ተጫዋቾች ታኑኪ ማሪዮን ወይም ሉዊጂ ጋላክሲን የመሳሰሉ ክላሲክ አልባሳትን መክፈት ይችላሉ።
የኒንቴንዶ ዓላማ ዝም ብሎ ጌሙን ድጋሚ ከመልቀቅ ያለፈ ነው፤ Super Mario Bros Wonder የSwitch 2 ጅማሮን እንዲመጥን ተደርጎ የተሰራ አንጋፋ ጌም ነው። በ2017 ለBreath of the Wild እንደተደረገው፣ አዲሱ ኮንሶል ቤተሰቦችን እና ቀንደኛ አድናቂዎቹን ሊማርክ የሚችል ትልቅ እና አንጋፋ ጌም ይዞ መጀመር ይፈልጋል።