icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

የሱፐር ማሪዮ ጋላክሲ እና ጋላክሲ 2 መውጫ ቀን ይፋ ተደረገ! 

ኒንቴንዶ ተወዳጆቹን ሱፐር ማሪዮ ጋላክሲን እና ሱፐር ማሪዮ ጋላክሲ 2ን ኒንቴንዶ ስዊች ላይ አንድ ላይ መጫወት የሚያስችል ጥቅልን እ.ኤ.አ. ኦክቶበር 2፣ 2025 ላይ እንደሚለቀቅ በይፋ አስታውቋል። በዓለም ዙሪያ በሚገኙ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተጫዋቾች ተወዳጅነትን ማግኘት የቻሉት እነዚህ ሁለት ታዋቂ ጌሞች የነባር እና አዲስ ተጫዎቾችን ልብ መግዛት በሚያስችል መልኩ ተዘጋጅተው በአዲስ መልክ ሊቀርቡ ነው!  

እ.ኤ.አ. በ2007 Wii ላይ የተለቀቀው ሱፐር ማሪዮ ጋላክሲ ክብ ቅርጽ ባላቸው ደረጃዎቹ፣ በፈታኝ የመሬት ስበት ኃይሉ እና በሚያስደንቅ የጠፈር ገጽታው የ3D ፕላትፎርም ጌሞችን መለወጥ ችሎ ነበር። በመቀጠል ተከታይ ክፍሉ እ.ኤ.አ. 2010 ላይ ለጨዋታ የበቃ ሲሆን አዳዲስ ፕላኔቶችን፣ በአዳዲስ ፈጠራዎች የተሞሉ መካኒክሶች እና ዮሺን በማካተት የመጀመሪያውን ክፍል ማስናቅ ችሎ ነበር። ሁለቱም ኒንቴንዶ ካዘጋጃቸው ድንቅ ስራዎች መካከል መመደብ እና እጅግ በርካታ ሽልማቶችን እና አድናቆትን ማትረፍ ችለዋል። 

ኒንቴንዶ ሁለቱንም ጌሞች በአንድ ጥቅል ማቅረቡ፤ ነባር ተጫዋቾች በጊዜ ሰረገላ ወደ ኋላ መመለስ እንዲችሉ፣ አዲስ ተጫዋቾች ደግሞ የዚህ አስደናቂ ተሞክሮ ተካፋይ እንዲሆኑ እድል ከመስጠቱም በላይ፣ የስዊች ቆይታን ማራዘም እና ስዊች 2ን በሰፊው ማስተዋወቅ ያስችላል። 

ይህ ድንቅ ጥምርታ ከመደበኛ ጥቅልነት ያለፈ ነው። ሁለቱም ጌሞች በተንቀሳቃሽ ሞድ 1080p እና ዶክ ሲደረግ ደግሞ 4K የሚደርስ የምስል ጥራት እና በሰከንድ 60 ፍሬሞች መጠቀም የሚያስችላቸው ቴክኒካል ማሻሻያ ተደርጎላቸዋል። እንዲሁም መቆጣጠሪያዎቹ ለስዊች እንዲመጥኑ ተደርገው የተስተካከሉ ሲሆን፣ ጆይ-ኮንን በመጠቀም የWiimote እንቅስቃሴዎችን ማስመሰል ወይም ነባሩ መቆጣጠሪያ መጠቀም ያስችላሉ። በተጨማሪም ኒንቴንዶ ተጫዋቾች በማንኛውም ጊዜ ሴቭ ማድረግ የሚችሉበትን አማራጭ አካቷል። 

ይህ ጥቅል ዝግጅቱን የበለጠ ልዩ ለማድረግ ተጨማሪ ይዘቶችንም ይዞ ይመጣል። የሳጋውን አስደናቂ የኦርኬስትራ ሙዚቃዎች መኮምኮም የሚያስችልዎ የሙዚቃ ስብስብ፣ የጌሙን እድገት የሚሳዩ አዳዲስ ንድፎችን የያዘ የስእሎች ስብስብ ተካተዋል። እንዲሁም ፈታኝ ተልዕኮዎችን ለሚሹ ተጫዋቾች የተነደፈ "ጋላክሲክ ቻሌንጅ" የተባለ አዲስ ሞድ እና ለማሪዮ እና ሮዛሊና አሚቦ የሚሆኑ አዳዲስ ማስጌጫዎች እና የተለያዩ ጉርሻዎች ይገኛሉ። 

መለቀቂያው ቀን እንዲሁ በዘፈቀደ የተመረጠ አይደለም። ኦክቶበር 2025 የሱፐር ማሪዮ ጋላክሲ 2 15ኛ ዓመት ነው። ይህን አስመልክቶም ኒንቴንዶ ሁለቱን ድንቅ ጌሞች አንድ ላይ ለተጨዋቾች በማቅረብ፣ ይህንን የስኬት ምዕራፍ ወደ ልዩ ክብረ በዓል ለመቀየር በማሰብ የወሰነው ውሳኔ ነው። 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !