icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ብላክ ኦፕስ 7 ቤታ ላይ የሚገኙ ምርጥ መሣሪያዎች!

ኮል ኦፍ ዲውቲ ብላክ ኦፕስ 7 ቤታ ላይ ለጥቃት፣ ለስልት እና ለመስክ ተልዕኮዎች የሚሆኑ ማሻሻያ መሣሪያዎችን መሞከር ያስችልዎታል። በተለይ የፈጣን ሞድ ጨዋታዎችን በበላይነት መቆጣጠር እንዲችሉ፣ የትኞቹን መሣሪያዎች መጠቀም እንዳለብዎ ማወቅ አስፈላጊ ነው። ከዚህ ቀጥሎ ቤታው ላይ የሚገኙ ምርጥ መሣሪያዎችን እንደ አጠቃቀማቸው እና ተወዳጅነታቸው በደረጃ አስቀምጠናል። 

ጥቃት (Lethal) 

ደረጃ - S 

  • Semtex፦ ጌሙን ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠረ ወሳኝ መሣሪያ ሲሆን፣ የተለያዩ ነገሮች ላይ መጣበቅ የሚችል በመሆኑ ምሽግ ውስጥ የተደበቁ ጠላቶችን ከተደበቁበት ተፍለክልከው እንዲወጡ ማድረግ የሚያስችል ወሳኝ መሣሪያ ነው።  

  • Frag grenade፦ ወሳኝ የቦምብ አማራጭ ቢሆንም፣ የፍንዳታ ቆይታው የሚዘገይ በመሆኑ አስተማማኝነት ይጎለዋል። 

  • Throwing knife፦ ጥቃት ላይ ለሚያተኩሩ ተጫዋቾች ጠላቶችን በፍጥነት መግደል የሚያስችል አማራጭ ነው። 

ደረጃ - A 

  • Proximity mine፦ በተለይ እንደ Domination ያሉ የመከላከል ተልዕኮዎች ተስማሚ ነው።  

  • Thermite፦ ሽፋን ይዘው የሚገኙ ጠላቶችን እና የተለያዩ ምሽጎችን ወይም መከላከያ ግንቦችን ድምጥማጥ ማጥፋት ያስችልዎታል። ሁለገብ ባይሆንም ትክክለኛ ሁኔታዎች ላይ ከተጠቀሙት እጅግ ውጤታማ ነው። 

 

ስልት (Tactical) 

ደረጃ - S 

  • Stun grenade፦ አሁንም ውጊያዎችን ማቋረጥ የሚያስችልዎ አሪፍ መፍትሄ ሲሆን፣ የጠላቶችን እንቅስቃሴ እና የማነጣጠር ብቃት ማዳከም የሚያስችል ጥቅም ይሰጥዎታል።  

  • Flash grenade፦ የተዘጉ ቦታዎችን መሰባበር ወይም ጠላቶች ላይ ጥቃት ማድረስ ያስችልዎታል። 

ደረጃ - A  

  • Stim፦ ጥቃት ላይ ለሚያተኩሩ ተጫዋቾች ወሳኝ መፍትሄ ሲሆን በፍጥነት ህይወትዎን ፈውሰው ወደ ውጊያ መመለስ ያስችልዎታል።  

  • Smoke grenade፦ ጥቅሙ እንደ ሁኔታው የሚለይ ቢሆንም፣ ከስናይፐር እይታ ለመሰወር ወይም ግቦችን ለማስጠበቅ ወሳኝ መፍትሄ ነው። 

የመስክ ተልዕኮ ማሻሻያዎች (Field Upgrades) 

ደረጃ - S 

  • Dead Silence፦ በድምጽ ራዳር እይታ ውስጥ ሳይገቡ ጥቃቶችን ማድረስ ያስችልዎታል። 

  • Portable Radar፦ አካባቢዎችን ለመቆጣጠር እና የጠላቶችን እንቅስቃሴ መተንበይ የሚያስችል ምርጥ መሣሪያ ነው። 

ደረጃ - A 

  • Munitions Box፦ ረጅም ጊዜ የሚወስዱ ጦርነቶች እና ዓላማ ላይ የተመሰረቱ ሞዶች ላይ የሚጠቀም ቢሆንም፣ Deathmatch ላይ ግን ያን ያህል አስፈላጊ አይደለም።  

  • Trophy System፦ በተለይ አጣብቂኝ ቦታዎች ላይ የቦምብ ጥቃትን መከላከል ያስችልዎታል። 

ደረጃ - B 

  • Recon Drone እና Jammer፦ በውጊያዎች ፍጥነት እና የቆይታ ጊዜ የተነሳ እዚህ ግባ የሚባል ጥቅም የሌላቸው ቢሆንም፣ ምናልባት ወደ ፊት ጌሙ በይፋ ሲለቀቅ ማስተካከያዎች ከተደረገባቸው የበለጠ ጥቅም ሊኖራቸው ይችላሉ። 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !