icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ሪማች ላይ የሚገኙ የተጫዋቾች ደረጃ ዝርዝር 

የሪማች የደረጃ አሰጣጥ በእልህ አስጨራሽ ፉክክሮች የተሞላ ሲሆን፤ የደረጃ እድገትዎን ለክቶ እና ከሌሎች ተጫዋቾች ጋር በማነፃፀር ደረጃ የሚሰጥዎት ሲስተምን ይከተላል። የትኛው ደረጃ ላይ እንደሚገኙ እና ደረጃዎን ከፍ ለማድረግ ምን ማሳካት እንዳለብዎ ለማወቅ የደረጃዎችን ዓይነት እና አሰራር ማወቅ አስፈላጊ ጉዳይ ነው። ከዚህ ቀጥሎ ሪማች ላይ የሚገኙ አጠቃላይ የደረጃዎች አይነትን ዝርዝር አዘጋጅተናል፦ 

ነሐስ (Bronze)፦ የውድድር ሞድ ላይ መግባት የሚያስችልዎ እና አብዛኛዎቹ አዳዲስ ተጫዋቾች የማጣሪያ ጨዋታቸውን ከጨረሱ በኋላ የሚጀምሩበት የመጀመሪያው ደረጃ ነው። እዚህ ደረጃ ላይ አብረዎት የሚጫወቱት ተጫዋቾች፣ በአጠቃላይ ጀማሪዎች ወይም መካከለኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ናቸው። በአጭሩ የጨዋታውን መሠረታዊ ነገሮች መማር እና ስልትዎን ማዳበር የሚችሉበት ጥሩ መነሻ ነው። 

ብር (Silver)፦ ይህ ደረጃ የተወሰኑ ክህሎቶችን ያዳበሩ እና ስልቶቻቸውን በጥቂቱ ማሻሻል የጀመሩ ተጫዋቾች የሚገኙበት ደረጃ ነው። 

ወርቅ (Gold)፦ ይህ ደረጃ ፉክክሮች ከሚታይባቸው ደረጃዎች አንዱ እና ነገሮች መጠጠር የሚጀምሩበት ነው። ይህ ደረጃ በአግባቡ የተደራጁ ተጫዋቾች የሚገኙበት፣ ጥቃቅን ስህተቶች ዋጋ የሚያስከፍሉበት እና ድል በቡድን አቀነጃጀት እና የካርታዎች ጥሩ ግንዛቤ ላይ የሚወሰንበት ነው። 

ፕላቲኒየም (Platinum)፦ ይህ ደረጃ ወደ ላቀ የውድድር ደረጃ የሚሸጋገሩበት ሲሆን፣ እዚህ ደረጃ ላይ የሚገኙ ተጫዋቾች ስለጌሙ ከፍተኛ እውቀት ያላቸው እና ቡድናቸውን በማደራጀት ሆነ ግቦቸውን በመንደፍ ረገድ የተካኑ ናቸው። 

ዳይመንድ (Diamond)፦ ይህ ደረጃ በጌሙን የተካኑ ተጫዋቾች የሚገኙበት ደረጃ ነው። እዚህ ደረጃ ላይ የሚደረሁ ግጥሚያዎች ከባድ እና ፈታኝ በመሆናቸው እያንዳንዱ ድል ወይም ሽንፈት የእድገት ሂደት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖን ያሳድራሉ። 

ማስተር (Master) እና ግራንድ ማስተር (Grand Master)፦ ይህ የጌሙ ከፍተኛው ደረጃ ሲሆን፣ ይህ ደረጃ ሪማች ውስጥ የሚገኙ የምርጦች ምርጥ፣ እንደልባቸው ጌሙን ማሾር የሚችሉ እና በማንኛውም ዘርፍ ጌሙ ላይ የነገሱ ተጨዋቾች የሚገኙበት የደረጃዎቹ ሁሉ መለኪያ እና የመጨረሻው ደረጃ ነው። 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !