icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ለምንድን ነው የዋርዞን ባትል ሮያል ሞድ፣ ብላክ ኦፕስ 7 ቤታ ላይ ያልተካተተው? 

በርካታ ተጫዋቾች ኮል ኦፍ ዲውቲ ብላክ ኦፕስ 7 ቤታ ላይ ዋርዞንን የመሞከር ትልቅ ፍላጎት የነበራቸው ቢሆንም፣ በሚያሳዝን ሁኔታ ፕሮግራሙ ውስጥ አልተካተተም ነበር። ከዚህ ቀጥሎ ባትል ሮያሉን መቼ መጫወት እንደሚችሉ እና ቤታው ላይ ያልተካተተበትን ምክንያት በዝርዝር ያገኛሉ። 

በቅድሚያ መገንዘብ ያለብዎ ጉዳይ፣ ብላክ ኦፕስ 7 በይፋ ለጨዋታ የሚበቃው እ.ኤ.አ ኖቬምበር 14፣ 2025 ላይ ሲሆን፣ የሙከራ ጨዋታው (Beta) መደበኛ መልቲፕለየር ሞድ እና ዞምቢ ሞድ ብቻ ያካተተ ስሪት ነበር። የቤታ ቆይታው የጦር መሳሪያዎችን፣ ካርታዎችን እና ዋና ዋና የጨዋታ መካኒኮችን ለመፈተሽ ታስቦ፣ ኦክቶበር መጀመሪያ ላይ የተካሄደ ቢሆንም ቀድሞውኑ ዋርዞንን ይህ ምዕራፍ ላይ የማካተት እቅድ አልነበረም። 

ዋናው ምክንያት ቀላል እና ቀጥተኛ ሲሆን፣ ዋርዞን የራሱ የሆኑ ግዙፍ ካርታዎች፣ ሉቶች፣ የኢኮኖሚ ሲስተም፣ እንዲሁም የጦር መሣሪያዎች ያሉት ራሱን የቻለ ሞድ ነው። ስለዚህ ዋርዞንን ቤታው ላይ ማካተት፣ የሙከራ ሂደቱን ማወሳስብ እና የሰርቨር መጨናነቅ ያስከትል ነበር። ለዚህ ነው አዘጋጆቹ ባትል ሮያልን ያለምንም እክል እና በጥሩ ሁኔታ ለጨዋታ ማብቃት እንዲችሉ ብቻውን መልቀቅ የመረጡት። 

ሌላው ምክንያት፣ ትሬያርክ እና የዋርዞን ቡድን በሁለቱ ሞዶች መካከል ያለውን ሚዛን መለየት መቻል መፈለጋቸው ነው። በተለይ የጦር መሳሪያዎች እና አባሪዎች ዙሪያ፣ መደበኛ መልቲ-ፕለየሩ ላይ የሚኖርዎት ተሞክሮ፣ ባትል ሮያሉ ውስጥ ከሚኖርዎት ጋር ፍጹም የተለየ ነው። ስለዚህ ይህ አካሄድ ቀሪው ጌም ሳይነካ ዋርዞንን በፍጥነት ማስተካክል ያስችላቸዋል። 

የመጨረሻው፣ ገበያን ያገናዘበ ምክንያት ነው። አክቲቪዥን እንደ አዲስ ካርታ፣ ልዩ መካኒክሶች እና የሲዝኑ አጠቃላይ እቅድ ያሉ የዋርዞን ይዘቶችን፣ እንደ Call of Duty NEXT ያሉ ልዩ ዝግጅቶች ላይ ማቅረብ መፈለጋቸው ነው። ቀድመው በወጡ መረጃዎች መሠረት፣ ዋርዞን ወዲያው እንደተጀመረ ብላክ ኦፕስ 7 ሲዝን 1 ላይ እንደሚካተት መረጃዎቹ ይገልፃሉ። እንዲሁም mastery camos እና አዳዲስ የጦር መሳሪያዎች ባትል ሮያሉ ላይ የሚካተቱም ይሆናል። 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !