
የCall of Duty: Black Ops 7 ቤታ ቅንብሮችዎን ማስተካከል የሚችሉበት አሪፍ አጋጣሚ ነው። እንደዚህ ፈጣን በሆኑ ጌሞች ላይ ጥሩ ማስተካከያዎችን መጠቀም ወሳኝ እና ከፍተኛ ለውጥን የሚያመጣ ጉዳይ ነው። በቤታ ቆይታዎ ጥሩ ተሞክሮ ማግኘት እንዲችሉ ቀጥለን ያስቀመጥናቸውን ቅንብሮች ዛሬውኑ ማስተካከል ይኖርብዎታል።
ኮምፒውተር ላይ የሚጫወቱ ከሆነ፣ የምስል ጥራቶች ላይ ከማተኮር ይልቅ፣ ለፍጥነት ቅድሚያ በመስጠት የግራፊክስ ቅንብሮችን በማስተካከል ይጀምሩ። በመቀጠል ጥላዎችን ይቀንሱ፣ እንዲሁም motion blur እና post-processing effects ያጥፉ። የጂፒዩዎ አቅም የሚፈቅድ ከሆነ ደግሞ፣ የአፈጻጸም ሞድን (performance mode) በማብራት፣ የፍሬም ፍጥነትዎ (framerate) ከፍተኛ ደረጃ ላይ እና የማይቆራረጥ መሆኑን ያረጋግጡ። እንዲሁም ወጥ የሆነ 120+ FPS የምስሎችን ፍጥነት በእጅጉ ያሻሽልልዎታል። ኮንሶል የሚጠቀሙ ከሆነ ደግሞ፣ የስክሪን ቅንብሮችዎ ውስጥ በመግባት የአፈጻጸም ሞድን (performance mode) ማብራትዎን ያረጋግጡ።
ለዚህ ተብሎ የተቀመጠ ልዩ ቁጥር ባይኖርም፣ ቤታው ላይ በርካታ ምርጥ ተጫዋቾች መቆጣጠሪያቸውን ከ 6 እስከ 8 እና የአግድም እና የቋሚ ማነጣጠሪያቸውን 1.0 ላይ በማድረግ ሲጠቀሙ ታይተዋል። ስናይፐር ወይም አውቶማቲክ መሣሪያ የሚጠቀሙ ከሆነ ደግሞ፣ ጥሩ ማነጣጠር እንዲችሉ Sensitivityዎን በትንሹ ቢቀንሱት ይመከራል። እንዲሁም፣ እንቅስቃሴዎን ያልተዛባ እና ፈጣን ለማድረግ፣ stick drift እንዳይፈጠር አድርገው deadzoneዎን በተቻለ መጠን እስከመጨረሻው ይቀንሱት።
የእግር ዱካዎች እና ሌሎች ድምፆችን በደንብ መስማት እንዲችሉ፣ ሙዚቃውን ያጥፉ ወይም ይቀንሱ። ከፍተኛ ፍሪኩዌንሲ ያላቸው ድምፆች ጎልተው እንዲሰሙዎት ደግሞ Headphones ወይም Boost Highን ይምረጡ። ይህ ቅንብር ጠባብ ቦታዎች ላይ ወይም ድምፆች ወሳኝነት በሚኖራቸው ቦታዎች ላይ ጠላቶችዎን ቀድመው መስማት ያስችልዎታል።
ጌሙን ለመጫወት የሚጠቀሙት መሳሪያ አቅም የሚፈቅድ ከሆነ Field of Viewን (FOV) ከ100 እስከ 110 በማድረግ ይጠቀሙ። ይህም ወደ ጎን የተሻለ ማየት እና ድንገት እንዳይከበቡ ለመከላከል ይረዳዎታል። ነገር ግን፣ በጣም ሰፊ የሆነ FOV ጠላቶችን አነስተኛ መስለው እንዲታዩ ሊያደርግ ስለሚችል፣ ከልክ በላይ አያስፉት። እንዲሁም፣ በማንኛውም ሁኔታዎች ወጥ የማነጣጠር ብቃት እንዲያገኙ ADS FOVን ያብሩ።
ጥቃት ላይ በማተኮር የሚጫወቱ ከሆነ slidingን አውቶማቲክ ላይ በማድረግ ይጠቀሙ፤ በውጊያዎች ወቅት ደግሞ ስህተቶችን ማስወገድ እንዲችሉ reload behavior priorityን ያብሩ። እንዲሁም፣ አንዳንድ ተጫዋቾች በወጥነት እና በተለዋዋጭነት መካከል ያለውን ሚዛናዊነት ለመጠበቅ aim assistን Standard ማድረግ ጠቃሚ እንደሆነ ገልፀዋል።
መልካም ጨዋታ!