icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ባትልፊልድ 6 ላይ የcrossplay አማራጭን ማጥፋት ይቻላል?

ባትልፊልድ 6 ሲሰራ በመደበኛነት crossplayን ያካተታል። ይህ ቴክኖሎጂ የኮምፒውተር፣ ፕለይ-ስቴሽን 5፣ እና ኤክስ-ቦክስ ሲርየስ ተጠቃሚዎችን አንድ ላይ መጫወት የሚያስች ነው። አሁን አሁን አብዛኛዎቹ የFPS ጌሞች ላይ የተለመደ ነገር ቢሆንም፣ በሁሉም ዘንድ ግን ተቀባይነት አላገኘም። አንዳንድ ከጓደኞቻቸው ጋር መጫወት የሚፈልጉ ተጫዋቾች ይህን ቴክኖሎጂ ቢያበረታቱም፣ ሌሎች ደግሞ መቆጣጠሪያ ጆይስቲክ እና ማውዝ-ኪቦርድ በሚጠቀሙ ተጫዋቾች መካከል ልዩነት መኖሩን እና በኮምፒውተር ተጠቃሚዎች ዘንድ የማጭበርበር ሂደትን ማባባሱን አልወደዱትም።  

ጌሙን ሲጭኑ crossplay በራሱ የሚበራ በመሆኑ፣ ሳያውቁት ማንኛውም ፕላትፎርም ላይ ከሚገኙ ተጫዋቾች ጋር ሊመደቡ ይችላሉ። ከEA አንፃር ስናየው፣ ተጫዋቾችን የማዛመድ ቆይታን ስለሚቀንስ እና የተጫዋች ማኅበረሰቡን የሚያዋህድ በመሆኑ ጠቃሚነቱ ግልጽ ጉዳይ ነው። ሁሉንም ተጫዋቾች አንድ ላይ ማስተናገድ ሰርቨሩ ሁሌም ሙሉ እንዲሆን ስለሚያስችለው፣ የማዛመድ ሂደቱን ቀላል ያደርገዋል። ሆኖም ግን ይህን አካሄድ ሁሉም አሜን ብሎ አልተቀበለውም፤ በተለይ የኮንሶል ተጫዋቾች ከኮምፒውተር ተጫዋቾች ጋር መጫወት አይፈልጉም። ምክንያታቸውም የኮምፒውተር ተጫዋቾች ማውዝ እና ኪቦርድ ስለሚጠቀሙ የተሻለ አፈፃፀም ወይም አባንስ ያገኛሉ የሚል ነው። 

እንደ እድል ሆኖ፣ ፕለይ-ስቴሽን 5 እና ኤክስ-ቦክስ ሲርየስ ላይ ማጥፋት ይቻላል። ወደ ጌሙ Settings በመግባት፣ System ወይም Configuration menu ውስጥ የCrossplay አማራጭ የሚገኝ ሲሆን፣ ጨዋታ ላይ ካልሆኑ ወይም matchmaking ካልጀመሩ ማጥፋት ይችላሉ። ይህን አማራጭ እንዳጠፉ፣ የmatchmaking ሂደቱ እርስዎ የሚጠቀሙት ፕላትፎርም ላይ ከሚገኙ ተጫዋቾች ጋር ብቻ ያዛምዳችኋል፣ PS5 ከPS5 ጋር ወይም Xbox ከXbox ጋር ብቻ ማለት ነው። ይህን በማድረግ ከኮንሶል ተጫዋቾች ጋር ሚዛናዊ እና ፍትሃዊ ጨዋታዎችን መጫወት ይችላሉ። 

አንድ ነገር ግን ያስታውሱ፣ Crossplayን ማጥፋት ሎቢ ላይ የሚገኙ ተጫዋቾችን ቁጥር በእጅጉ ይቀንሳል፣ ይህም ብዙ ተጫዋቾች ኦንላይን በማይኖሩበት ወቅት ረጅም ሰዓት መጠበቅ ሊኖርብዎ ይችላል። ስለዚህ ምቾትዎ፣ የጨዋታ ሂደትዎ ላይ ተጽዕኖ እንዳይፈጥር፣ ነገሮችን ማመጣጠን ይኖርብዎታል። EA በበኩሉ ያለምንም ጥበቃ ቶሎ ተጫዋቾች ጋር መዛመድ እንዲችሉ crossplay ማብራትን ይመክራል፣ ነገር ግን ምርጫው ሙሉ በሙሉ የራስዎ ነው። 

ኮምፒውተር ላይ ያለው ሁኔታ ግን የተለየ ነው። Crossplayን ማጥፋት አይችሉም። ኮንሶሎች ላይ የሚገኘው ማጥፊያ መንገድ፣ ሜኑ ውስጥ፣ EA መተግበሪያ ወይም ስቲም ላይ አልተካተተም። ሁሉም የኮምፒውተር ተጠቃሚዎች፣ ሌሎች ፕላትፎርሞች ላይ ከሚገኙ ተጫዋቾች ጋር የሚመደቡ ሲሆን፣ ይሄ ደግሞ በብዙ ተጫዋቾች ዘንድ ተቀባይነትን አላገኘም። ተጫዋቾች ሬዲት እና የEA ፎረሞች ላይ፣ Crossplayን ማጥፋት የሚችሉበት አማራጭ እንዲካተት በተደጋጋሚ ጥያቄ ያቀረቡ ቢሆንም፣ እስካሁን ከአዘጋጆቹ የተሰጠ ምንም ምላሽ የለም። 

ሌላው ጉዳይ፣ ባትልፊልድ 6 consoles-only crossplay የሚባል ሞድ የለውም። ለምሳሌ፡- የCrossplay አማራጭን PS5 ላይ ካጠፉት፣ ከXbox ተጫዋቾች ጋር መጫወት አይችሉም። እያንዳንዱ ፕላትፎርም ለብቻው የቆመ በመሆኑ፣ የሃርድዌር ችግሮችን ለማስወገድ ይረዳል፤ ነገር ግን የተለያዩ ኮንሶሎች ላይ የሚገኙ ተጫዋቾች አብረው መጫወት እንዳይጫወቱ ይዳርጋል። 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !