
ባትልፊልድ 6 ላይ "Content Not Installed" የሚለው የብልሽት መልዕክት ብዙዎችን ያሰለቸ ጉዳይ ነው። ጌሙን በአግባቡ ጭነው፣ መልቲ-ፕለየር ለመጫወት ሲሞክሩ “Purchase this content to play” የሚል የብልሽት መልዕክት በተደጋጋሚ ይመጣልዎታል? አያስቡ! እርስዎ የሰሩት ምንም ጥፋት የለም። ይህ ብልሽት ጌሙን ሲከፍቱ የሚፈጠር የEA ሰርቨር ወይም የlicense ችግር ነው።
ይሄ ብልሽት ብዙውን ጊዜ በሰርቨሮች መጨናነቅ ምክንያት የሚፈጠረ ነው። በርካታ ተጫዋቾች ጌሙን ሲከፍቱ የEA ሰርቨሮች ስለሚጨናነቁ፣ ጌሙ በአግባቡ መስራት ይሳነዋል። በዚህም ምክንያት የEA መተግበሪያ ወይም Steam፣ multiplayer በትክክል መጫኑን ለማወቅ ስለሚቸገር፣ ይሄን የስህተት መልዕክት ያሳያል። ይህ ችግር ኮንሶል ተጠቃሚ ከሆኑት ይልቅ ጌሙን ኮምፒውተራቸው ላይ ቀድመው የጫኑ ተጫዋቾች ላይ የሚከሰት ብልሽት ነው።
ባትልፊልድ 6 እንደ ዝግጅቶች፣ multiplayer፣ texture packs፣ ያሉ የተለያዩ ክፍሎች ያሉት በመሆኑ፣ የማጣራት ሂደቱ ከእነዚህ አንደኛው ላይ ስህተር ያጋጥመዋል። ስለዚህ አስፈላጊ ነገሮች ሁሉ በትክክል ቢጫኑም እንኳን ሲስተሙ multiplayer የለም ብሎ ሊደመድም ይችላል።
ጌሙ ሲከፈት የሚኖሩ ጫናዎች ነገሩን የሚያባብሱ ሲሆን፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ተጫዋቾች በተመሳሳይ ጊዜ login ለማድረግ በሚሞክሩበት ወቅት፣ የEA ሰርቨሮች ስለሚጨናነቁ፣ ትዕዛዞችን ማስተናገድ ይሳናቸዋል። የEA መተግበሪያ licenses በተናጠል የሚፈትሽ በመሆኑ፣ አንዴ ሞክሮ ሂደቱ ካልተሳካ ወደ ጌሙ እንዳትገቡ ይከለክላችኋል።
EAዎች በበኩላቸው ችግሩን ለመቅረፍ እየሰሩ እንደሆነ አሳውቀዋል። እስከዛው ነገሮችን እስከሚስተካከሉ ግን እነዚህን ጊዜያዊ መፍትሄዎች መሞከር ይችላሉ፦ ጌሙን እና የEA መተግበሪያውን (ወይም Steamን) አጥፍተው ድጋሚ ያብሩ። የEA መተግበሪያን በመጠቀም የጌሙን installationን ያስተካክሉ። ጌሙን እና ላውንቸሩን ያዘምኑ። Installation settings ውስጥ የሚገኘው multiplayer module sync እንዲያደርግ አብርተው ያጥፉት። ጌሙ ውስጥ የሚገኘውን browser በመጠቀም ሰርቨሩን በቀጥታ ለመቀላቀል ይሞክሩ። የዘረዘርናቸው መፍትሄዎች ካልሰሩ የመጨረሻ አማራጭዎ ጌሙን አጥፍተው ድጋሚ መጫን ነው፣ ይህ ማለት ግን ሁሉንም ነገር ያስተካክልልዎታል ማለት አይደለም። እንዲሁም፣ የኢንተርኔት መቆራረጥን ለማስወገድ፤ ባለገመድ የኢንተርኔት ግንኙነት ይጠቀሙ።
ለጊዜው፣ ሙሉ በሙሉ ችግሩን የሚፈታ አስተማማኝ መፍትሄ ባለመኖሩ፣ በትዕግስት መጠበቅ ይመከራል። EA ሰርቨሮቹን በቅርቡ የሚያስተካከል በመሆኑ፣ ነገሮች በቅርቡ ወደ መደበኛ አቋማቸው ይመለሳሉ። በአጭሩ "Content Not Installed" የሚል ነገር ካዩ አይደናገጡ፣ ችግሩ ከባትልፌልድ 6 ላውንቸር እንጂ ከእርስዎ አይደለም።