
SV-98 ባትልፊልድ 6 ውስጥ ከሚገኙ ምርጥ እና አደገኛ ስናይፐሮች መካከል አንዱ ነው። ይህ መሳሪያ በአንድ ተኩስ ብቻ የጠላት ግንባርን መበታተን ለሚፈልጉ ተጫዋቾች አስደናቂ ምርጫ ነው። ከእርስዎ የሚጠበቀው በአግባቡ አነጣጥረው መተኮስ ብቻ በመሆኑ፣ ክፍት አካባቢዎች ላይ ጠላቶች አጠገብ መሆን ሳይጠበቅብዎ ከርቀት መረፍረፍ ያስችልዎታል። SV-98 እጅግ አስተማማኝ፣ አስጨናቂ እና በብቃት ከተጠቀሙበት ደግሞ ጠላቶችን ከመዘረር ወደ ኋላ የማይል በመሆኑ፣ የRecon (ሰላይ) ሚና የሚጫወቱ ከሆነ የግድ ሊኖርዎ የሚገባ አንጀት አርስ መሳሪያ ነው።
የዚህን መሳሪያ ሙሉ አቅም መጠቀም እንዲችሉ፣ አንዳንድ ማስተካከያዎችን ማድረግ ይጠበቅብዎታል። ማስተካካያዎቹን ማድረግ ያስፈለገበት ምክንያትም፣ ጥይቱ መጓዝ የሚችለውን ርቀት፣ አስተማማኝነቱን እና የተኩስ ፍጥነቱን እንቅስቃሴዎ ሳይገደብ ለመጨመር እና ሙሉ አቅሙን ጥቅም ላይ ለማዋል ነው።
SV-98 ጋር አብረው እንዲጠቀሟቸው የሚመከሩ የምርጥ አባሪ መሳሪያዎች ዝርዝር እነሆ፡-
Scope (ማነጣጠሪያ መነጽር)፦ S-VPS 6X
Muzzle (አፈሙዝ)፦ Dual Muzzle Brake
Barrel (ቧንቧ)፦ 3LR 730mm Long Barrel
Underbarrel (ከታች የሚገጠም ቧንቧ)፦ Bipod
Magazine (ካርታ/ካዝና)፦ ባለ 10-ዙር (default mag)
Ammunition (ጥይት)፦ Long-Range Rounds
Optic Accessory (ተጨማሪ ማጉያ መነጽር): Anti-Glare Filter
Ergonomics (ማመቻቻ)፦ Straight-Pull Bolt
እነዚህን አባሪ መሳሪያዎች መጠቀም የSV-98 ስናይፐርዎን አቅም እና አስተማማኝነት እጅጉኑ ያሳድጋል። እንዲሁም Bipod እና straight-pull boltን በመጠቀም፣ በደረትዎ መሬት ላይ ተኝተው በቀላሉ ማነጣጠር እና ዒላማዎን ሳይስቱ በተከታታይ ጠላቶችን መግደል ያስችልዎታል።
የRecon (ስለላ) ሚና ለስናይፐር ተብሎ የተዘጋጀ በመሆኑ የስለላ ሚናዎን እንዳይቀይሩ። ይህም ሲያነጣጠሩ እና ጠላትን ዒላማ ውስጥ ሲያስገቡ ተጨማሪ ጉርሻዎችን ያስገኝልዎታል። እንደ ተቀያሪ መሳሪያ ደግሞ ቀላል ክብደት፣ ፍጥነት፣ እና ቅርብ የሚገኙ ጠላቶችን ዋጋ መስጠት የሚያስችለውን ES-5.7 ቢጠቀሙ ይመከራል።
ተወርዋሪ መሳሪያዎችን በተመለከተ ደግሞ፣ በደፈጣ የሚደረጉ ጥቃቶችን አስቀድመው ማወቅ እንዲችሉ Proximity Sensor፤ እንዲሁም ድምጽ ሳያሰሙ በድብቅ ጠላቶችን ለማጥቃት ደግሞ ተወርዋሪ ጩቤዎችን ይጠቀሙ።
የጦር አውድማዎች ላይ SV-98ን መጠቀም፣ ስልታዊ ቦታ መምረጥን እና ታጋሽነትን ይጠይቃል። ሁሌም ቢሆን ከፍታ ያላቸው ወይም ክፍት የሆኑ ቦታዎችን መያዝ፣ ዒላማዎን ግልጽ እይታ ውስጥ ማስገባት፣ እና የተወሰኑ ጥቃቶችን ከጣሉ በኋላ ወዲያው ቦታ ቀይረው መደበቅ መቻል አለብዎ። እንዲሁም በቻሉት መጠን Bipodን ይጠቀሙ። የዚህ ስናይፐር ድምጽ እና ተኩስ እጅግ ፈጣን በመሆኑ ዒላማዎን መምታት ሊያስጨንቅዎ የሚገባ ጉዳይ አይደለም። እንዲሁም፣ በፍጥነት ማቀባበያ ስልቶቹን ጊዜ ሰጥተው ከተለማመዷቸው፣ ጠላቶችዎ ከየት እንደተተኮሰባቸው እንኳን ሳይያውቁ በየተራ መለቃቀም ያስችልዎታል።
በመጨረሻም፣ የሚገኙበት ቦታ ርቀት በጨመረ ቁጥር ጥይቱ ምን ያህል አንግል ዝቅ እንደሚል እና ምን ያህል የመጓዝ አቅም እንዳለው መረዳት እንዲችሉ ደጋግመው ቢለማመዱ ይመከራል። እነዚህን በደንብ ከተለማመዱ እንቅስቃሴ ላይ የሚገኙ ዒላማዎችን ሁሉ ሳይቀር በቀላሉ ጭንቅላታቸውን የመበታተን ብቃት ይኖርዎታል።
መልካም ጨዋታ!