icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ባትልፊልድ 6 ላይ የቅርብ ርቀት ውጊያዎችን መቆጣጠር የሚያስችሉዎ፣ የTR-7 ምርጥ አባሪ መሳሪያዎች 

TR-7 ባትልፊልድ 6 ላይ የሚገኝ አስደናቂ ተከታታይ ተኩሶችን የማድረግ አቅም ያለው ሁለገብ ጠመንጃ ነው። ይህ መሳሪያ ለቅርብ ርቀት ውጊያዎች የሚሆን አሪፍ አማራጭ ሲሆን፣ መካከለኛ ርቀቶች ላይ ለሚደረጉ ውጊያዎችም አጥጋቢ ውጤትን ያስገኛል። ዒላማዎችን ማጥቃት፣ ጠላቶችን ማሸሽ፣ ተቃራኒ ቡድኖች ላይ የማያቋርጥ ጫና መፍጠር ለሚፈልጉ ተጫዋቾች የሚሆን ሁነኛ መሳሪያ ነው። 

TR-7 በአግባቡ ከተስተካከለ እና ጥቅም ላይ ከዋለ ጠጅ እንደቀመሰ SMG፣ እጅግ ፈጣን፣ አስተማማኝ እና ጠባብ ቦታዎች ላይ ጠላቶችን ማስጨነቅ የሚችል ገዳይ መሳሪያ ነው። ይህ በፉክክር የተሞላ ጌምን በበላይነትን ለመምራት፣ የTR-7 ተንቀሳቃሽነትን፣ በተኩስ ወቅት የሚኖረው የእርግጫ መጠንን እና በተከታታይ ጠላቶችን የመረፍረፍ አቅሙን ማሳደግ ያስፈልጋል። 

TR-7 ጋር ሊጠቀሟቸው የሚገቡ ምርጥ አባሪ መሳሪያዎች፡ 

  • ኦፕቲክ፦ 1X Mini Flex 

  • ከታች የሚገጠም ቧንቧ፦ Magazine Stop 

  • ጥይት፦ Hollow Point 

  • ካርታ/ካዝና፦ 20-Round Quick Mag 

  • ቧንቧ፦ Short 432mm or Fluted 

  • አፈሙዝ፦ Close-Combat Suppressor 

 

ይህ አወቃቀር TR-7 ሙሉ አቅሙን ለመጠቀም የሚያስፈልጉትን ነገሮች በሙሉ በማቅረብ፣ ግልጽ እይታ፣ ፈጣን የማቀባበል አቅም እና እንደልብ ተንቀሳቃሽ ያደርጉታል። እነዚህን አባሪ መሳሪያዎች በመጠቀም ዒላማዎችን በፍጥነት ማጥቃት፣ ጠላቶችን ወደኋላ ማሸሸት እና ትንሹ ካርታ ላይ ሳይታዩ ጥቃቶችን ማድረስ ይችላሉ። 

TR-7 ሦስት ዋና ዋና ክፍሎች ላይ ያተኩራል፡- 

1.  ተንቀሳቃሽነት (Total Mobility) 

መንቀሳቀስ በፍፁም ማቆም የለብዎትም። TR-7 በድብቅ ለሚደረጉ ጥቃቶች ሳይሆን የተሰራው፣ ጠላቶች ላይ ድንገተኛ እና ቀልጣፋ ጥቃቶችን ለማድረስ ነው። ቅልጥፍናዎን በመጠቀም ኮሪደሮች እና ጠባብ ቦታዎችን በቁጥጥርዎ ስር ያውሉ። 

2.  የእርግጫ መጠኑን ይቆጣጠሩ (Recoil Control) 

በሚተኩሱበት ወቅት መሳሪያው የሚፈጥረው እርግጫ ቀላል ቢሆንም፣ ነገር ግን ቀስ በቀስ ይጨምራል። ስለዚህ ጊዜ ወስደው እርግጫውን እና መቆጣጠር የሚችሉባቸውን ስልቶች ይለማመዱ። ከጥቂት ልምምድ በኋላ፣ እየሮጡ ቢተኩሱ እንኳን ዒላማዎ ሳይዛነፍ ሙሉ የጥይት ካርታ መጨረስ ይችላሉ። 

3.  አካባቢን ያማከለ አጠቃቀም (Map Adaptation) 

ክፍት የሆኑ ካርታዎች ላይ አስተማማኝነቱን ለመጨመር Fluted ቧንቧ እና High-Velocity ዙሮችን ይጠቀሙ። ዝግ ካርታዎች ላይ ደግሞ በቅልጥፍና መጠቀም እንዲችሉ Short ቧንቧ መጠቀምዎን ይቀጥሉ። እንዲሁም ድምጽዎን አጥፍተው ለመንቀሳቀስ የቅርብ ርቀት ውጊያ ድምጽ ማፈኛን በማጣመር ይጠቀሙ። 

ማቀባበል በሚኖርብዎት ወቅት እንደ ES-5.7 ያለ ቀላል ተቀያሪ መሳሪያ ይጠቀሙ። 

በመጨረሻም ማንኛውም ዝመናዎች ከተደረጉ በኋላ አባሪ መሳሪዎችዎን ማስተካከልዎን ያረጋግጡ። የባትልፊልድ 6 የጦር መሳሪያዎች አጠቃቀም ብዙውን ጊዜ የሚቀያየር በመሆኑ፣ ትንሽ የምትባለው ማስተካከያ መዛባቷ ብቻ ትልቅ ተጽዕኖ ልትፈጥር እና የመሳሪያዎን አቅም ልታዳክም ትችላለች።  

መልካም ጨዋታ! 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !