
የባትልፊልድ 6 መለቀቅን ተከትሎ እንደተለመደው “የትኞቹ ናቸው ምርጥ መሳሪያዎ?” የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም። የጀማሪዎችን ይሁን ወይም ልምድ ያካበቱ ተጫዋችን፣ የአጨዋወት ዘይቤ የሚመጥኑ ምርጥ መሣሪያዎች ይገኛሉ። ደረጃዎን መሠረት በማድረግ የጦር መሳሪያዎችን መምረጥ እንዲችሉ፣ የተሟላ የምርጥ መሳሪያዎች ምድብ ዝርዝር ቀጥለው ያገኛሉ።
የጌሙ መጀመሪያ ላይ የሚገኙ መሳሪያዎች ቁጥር ውስን ቢሆንም፣ አቅማቸው ግን እጅግ አስደናቂ ነው። የጌሙ መጀመሪያ ከሚገኙ ቀላል መሳሪያዎች መካከል፣ SOR-556 MK2 አንዱ ምርጥ አማራጭ ሲሆን፣ አስተማማኝ እና ሁለገብ የሆነ ጠመንጃ ነው። በፍጥነት የመተኮስ አቅም ባይኖረውም፣ መካከለኛ ርቀት ውጊያዎች ላይ ጉዳት የማድረስ አቅሙ ከፍተኛ ነው። እንደልብዎ መቆጣጠር እንዲችሉ እና አስተማማኝነቱን ለመጨመር ከረጅም አፈሙዝ እና bipod አጀታ ጋር በማጠመር ይጠቀሙበት።
ሌላው የጌሙ ጅማሮ ላይ ሊጠቀሙት የሚገባ ምርጥ መሣሪያ K30 SMG ነው። የታመቀ ጉልበት እና ፈጣን ተኩስ ያለው በመሆኑ፤ ለአጭር ርቀት ውጊያዎች የልብ አድርስ ነው። አነስተኛ እርግጫ እና በፍጥነት የሚቀባበል በመሆኑ ከተማ ውስጥ እና የተጨናነቁ ቦታዎች ላይ ተከታታይ ጥቃቶችን ማድረስ ያስችልዎታል። በአጭሩ፣ የጌሙ ጅማሮን የሚመጥን እና ውድድሮችን በፍጥነት ለማለፍ የሚረዳ አሪፍ መሳሪያ ነው።
ለርቀት የሚሆኑ መሳሪያዎችን የሚፈልጉ ከሆነ ደግሞ MCS-880 ምርጫዎ ሊሆን ይገባል። semi-automatic ሞዱ እና ከረዥም ርቀቶች ጥቃት ማድረስ ማስቻሉ ግቦችዎን በሚጠብቁበት ወቅት እጅግ ይጠቅምዎታል። እንዲሁም የቤት ውስጥ ውጊያዎች ወቅት ከመካከለኛ ደረጃ ጠመንጃዎች ጋር የሚመጣጠን አገልግሎት ይሰጣል።
በርካታ መሳሪያዎችን እና አባሪዎችን ማስከፈት ሲጀምሩ ጌሙ በከፍተኛ ሁኔታ መቀየር ይጀምራል። እንደሚታወቀው M8A1 ከብላክ ኦፕስ 2 ጀምሮ የሚታወቅ መሳሪያ ሲሆን፤ አሁንም በአስደናቂ ሁኔታ ድጋሚ ተመልሷል። ይህ መሳሪያ በአንድ ተኩስ ብቻ ጠላቶችን ማስወገድ የሚችል ሲሆን፣ የቡድን ውጊያዎች ላይ ከባለ 2x ማነጣጠሪያ መነጽር እና ረጅም አፈሙዝ ጋር በማጣመር ሲጠቀሙት ደግሞ አስደናቂ ውጤት ያስገኝልዎታል።
ሌላኛው የጌሙ መገባደጃ ላይ የሚያገኙት ወሳኝ መሳሪያ ደግሞ DRAVEC 45 ነው። ይህ አስደናቂ SMG መሳሪያ እጅግ በጣም ፈጣን እና አስተማማኝ የተኩስ ፍጥነት ያለው ሲሆን፣ ተጨማሪ የጥይት ካርታ ሲጨመርለት ደግሞ አቅሙ በአስደናቂ ሁኔታ ይጨምራል። በአጭር ርቀት ውጊያዎች ወቅት ከአብዛኞቹ ጠመንጃዎች ጋር እኩል መወዳደር መቻሉ እና ለአያያዝ ቀላልና ምቹ መሆኑ ደግሞ የጥቃት ተልዕኮዎች ላይ አትኩረው ለሚጫወቱ ተጫዋቾች እጅግ ተስማሚ ነው።
ከባድ ከሚባሉት የጦር መሳሪያዎች መካከል ደግሞ PKP Pecheneg በከፍተኛ የተኩስ አቅሙ ይታወቃል። የጌሙ መገባደጃ ላይ የሚገኙ ትጥቆች እና ትክክለኛዎቹን አባሪ መሳሪያዎች ከገጠሙለት ደግሞ ጥይቶች ይተኩሳል ሳይሆን ያርከፈክፋል ቢባል ማጋነን አይሆንም። በተለይ ፈጣን ተኩሶች ወሳኝነት በሚኖርባቸው እንደ defensive ወይም siege ያሉ ሞዶች ላይ ትልቅ ሚናን ይጫወታል።
በመጨረሻም፣ ምርጥ ከሚባሉ ባለማነጣጠሪያ መሳሪያዎች (sharpshooters)፤ SVK DMR ለመካከለኛ ርቀት ውጊያዎች የማያወላውል አማራጭ መሆኑን አስጠብቆ ቀጥሏል። ከፍተኛ ጉዳት የማድረስ አቅም ያለው በመሆኑ፣ ግዴታ 300 ሜትር ያህል መጠጋት ሳይኖርብዎ በፍጥነት ጠላቶችን መለቃቀም ያስችልዎታል።