icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ባትልፊልድ 6 ላይ በርካታ XPዎችን መሰብሰቢያ አስደናቂ መንገዶች 

ባትልፊልድ 6 ላይ በፍጥነት ደረጃዎን ማሳደግ እና በቀላሉ መሳሪያዎቻችን ማስከፈት ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ፣ ምን ዓይነት ዘዴዎችን መጠቀም እንዳለብዎ እና በአጭር ጊዜ ውስጥ በርካታ XPዎችን ማግኘት እንደሚችሉ ከዚህ ቀጥሎ በዝርዝር አዘጋጅተንልዎታል። 

1.  ሞድ አመራረጥ፦ Conquest እና Breakthrough እጅግ በጣም ብዙ ጠላቶች፣ በርካታ ተልዕኮዎች እና ከፍተኛ XPዎችን ማግኘት የሚችሉባቸው ምርጥ ሞዶች ናቸው። ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆኑ፣ Portal Mode ውስጥ ወደ ሚገኘው Extreme Conquest በመግባት፤ አንድ የጠላት ባንዲራን በመውሰድ እስከ 1,000 የሚደርሱ XPዎችን ማግኘት የሚችሉ ሲሆን፣ ይህም አስር መደበኛ ግድያዎችን አድርገው ከሚያገኙት ጋር እኩል ነው። እንዲሁም ትኩረትዎን ተልዕኮዎች ላይ በማድረግ፤ በፍጥነት ደረጃዎን ማሳደግ ይችላሉ። 

2.  ብቻዎን አይጫወቱ፦ ጌሙ የተቀናጀ የቡድን ስራን የሚከተሉ ተጫዋቾችን ያበረታታል። በቡድን ሲጫወቱ ወደ 5% ገደማ ተጨማሪ የXP ጉርሻ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን፤ የቡድን አጋሮችዎን ከፈወሱ ወይም ከረዱ ደግሞ ከዚህ የበለጠ ማግኘት ይችላሉ። የሚያደርጓቸው እያንዳንዱ ፈውሶች፣ እርዳታዎች ወይም የጥይት አቅርቦቶች ከፍተኛ መጠን ያለው XP ያስገኝልዎታል። ከቡድንዎ ጋር በመሆን ተልዕኮዎችን በመወጣት እና የቡድን ትዕዛዞችን በመስጠት የXP ሽልማትዎን በእጥፍ ይጨምሩ። 

3.  ውድድሮች ላይ ይሳተፉ፦ በየቀኑ 5 AM ላይ የሚጀምሩ እና በድምሩ 10,000 XP የሚያስገኙ 3 ተልዕኮዎች ይገኛሉ። ደረጃ 20 ላይ ሲደርሱ ደግሞ ሳምንታዊ ተልዕኮዎች የሚከፈቱ ሲሆን፣ በዚህም እስከ ወደ 60,000 የሚጠጉ XPዎችን መሸለም ይችላሉ። በአጭሩ ያለምንም ድካም እና በአነስተኛ ጥረት በሳምንት ከ130,000 በላይ XPዎችን ማግኘት ይችላሉ። ትኩረትዎ እንዳይበተን፣ Menu ውስጥ ሂደትዎን መከታተልዎን ብቻ አይርሱ። 

4.  XP Boosters ይጠቀሙ፦ ለጊዜው Experienceዎን በእጥፍ መጨመር ስለሚያስችሉዎ፣ ማንኛውንም ውድድር ከማድረግዎ በፊት፣ ቦነስ አካውንት፣ መሣሪያ ወይም የተሽከርካሪ XP ቶክኖች፣ እንዳሉዎ ቀድመው ያረጋግጡ። ብዙውን ጊዜ መግቢያው ላይ ባሉ ተልዕኮዎች ወይም ውድድሮች አማካኝነት ያገኟቸዋል። እንዲሁም ከPortal Session ጋር በማቀናጀት የXP መጠንዎን በፍጥነት መጨመር ይችላሉ። 

ተጨማሪ ዘዴዎች፦ 

EA Double XP Weekend ላይ መሳተፍ ነፃ Boost የሚያስገኝልዎ ሲሆን፤ Medic ወይም Support ሚናዎችን በመምረጥ እና የቡድን አጋሮችዎን በመፈወስና በመርዳት ደግም ይበልጥ ዳጎስ ያለ ሽልማት ማግኘት ይችላሉ። በጥረቴ ነው XPዎችን ማግኘት የምፈልገው ካሉ ደግሞ፣ Breakthrough vs. Bots ላይ በቀላሉ Kill Chains እና XPዎችን ማግኘት ይችላሉ። 

በአጠቃላይ ባትልፊልድ 6 ላይ በፍጥነት ደረጃዎን ማሳደግ የሚችሉባቸው ቀላል ዘዴዎች፦ Portal + የቡድን ጨዋታ + ውድድሮች + Boosters ናቸው። እነዚህን በመጠቀም ዛሬውኑ በርካታ XPዎችን መሰብሰብ፣ መሳሪያዎችን መክፈት፣ እና ባትልፊልድ ላይ አይበገሬ መሆን ይችላሉ! 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !