icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ፎርትናይት ላይ (R.E.P.O) ስኪኖችን ማግኛ መንገዶች እና መሸጫ ዋጋቸው 

(R.E.P.O) ስኪኖች የፎርትናይት Gaming Legends Series አካል ናቸው። ለመጀመሪያ ጊዜ የወጡት ምዕራፍ 6 ሲዝን 4 ላይ ሲሆን፣ ይሄ ልዩ ስብስብ በወቅቱ በነበረው የቴክኖ-ሆረር ጭብጥ (techno-horror theme) እና የወደፊቱን ዓለም በሚያንፀባርቅ ዲዛይኑ የተነሳ የተጫዋቾችን ቀልብ በቀላሉ መሳብ ችሏል። 

የ(R.E.P.O) ጥቅል በቀጥታ በዕቃ መደብሩ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፣ ይሄ ጥቅል የEpic Games ፕሪሚየም ስብስቦች መካከል አንዱ ሲሆን ዋጋውም 1,800 V-Bucks ነው። በውስጡ ከሚይዛቸው ነገሮች አንፃር ሲታይ ዋጋው ትንሽ ከፍ ያለ ቢሆንም ዋጋውን የሚመጥኑ ነገሮችን አካቷል። ጥቅሉ የሚከተሉትን ያካተታል፥- 

  • ዋናው ስኪን (R.E.P.O) ሴሚቦት (Semibot)፣ ሮቦቲክ ሪከቨሪ ዩኒት 

  • ተመሳሳይ ሜካኒካል ማጌጫ ቦርሳ (Back Bling) 

  • የኢንዱስትሪ መከትከቻ (Pickaxe) 

  • ተመሳሳይ ብረታማ ንድፍ ያለው የጦር መሳሪያ መጠቅለያ (Weapon Wrap) 

ይሄን ጥቅል ለማግኘት ወደ መደብሩ እስኪመለስ መጠበቅ ብቻ ነው የሚጠበቅብዎ። ለመጀመሪያ ጊዜ ፎርትናይትማሬስ 2025 (Fortnitemares 2025) ላይ ነው የወጣ ሲሆን፤ ይሄም በየዓመቱ ጌሙ ላይ የሚከበር የሃሎዊን (Halloween) በዓል ሲሆን ይህ ወቅት ሲመጣ ወደ መደብሩ እንደሚመለስ ይጠበቃል። ለማስክፈት ምንም ልዩ ተልዕኮዎች መወጣት ወይም ወድድር ማድረግ አያስፈልግም። በቀጥታ V-Bucksዎን በመጠቀም መግዛት ይችላሉ። 

ሙሉውን ጥቅል መግዛት የማይፈልጉ ተጫዋቾች እቃዎቹን በተናጠል መግዛት ይችላሉ። (R.E.P.O) ሴሚቦት (Semibot) ስኪን ብቻውን 1,500 V-Bucks የሚያወጣ ሲሆን፣ የተቀሩት ተጨማሪ እቃዎች ደግሞ ከ300 እስከ 500 V-Bucks ያወጣሉ። ዋጋቸው ቋሚ ቢሆንም፣ የመግኘት አዝማሚያቸው የሚወሰነው በዕቃ መደብሩ ፕሮግራም ነው። 

ይህ የ(R.E.P.O) ጥቅል ልዩ ዲዛይን ያለው ሲሆን፦ ቀይ እና ሰማያዊ የሚያበሩ ኤፌክቶች ያሉት፣ ግማሽ ሰው፣ ግማሽ ሳይበርኔቲክ (cybernetic) መልክ እና የሳይንስ ልብወለድ ወይም የሳይበርፐንክ (cyberpunk) ገጽታ አለው። እንደ Doom፣ Halo፣ እና Resident Evil የመሳሰሉት ታዋቂ ፍራንቻይዝ ገጸ-ባህሪያት ጎን ለጎን የGaming Legends Series ጥበባዊ የፈጠራ አቅጣጫን ተከትሎ የቀረበ ነው። 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !