icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ፖኪሞን ሌጀንድስ፡ ዜድ-ኤ ላይ ቅሪተ አካል የሆኑ ፖኪሞኖችን (አማውራ፣ ታይራንት እና ኤሮዳክቲል) እንዴት ማግኘት ይቻላል? 

በቅድሚያ ቅሪተ አካልን ወደ ነበረበት መመለስ የሚችሉት ዋናውን ተልዕኮ 10 ማለትም (The Secrets of Mega Evolution) ካጠናቀቁ በኋላ በመሆኑ ዋናውን ታሪክ ማጠናቀቅ የግድ ይኖርብዎታል። ይህን ተልዕኮ ከጨረሱና ደረጃ F ከደረሱ በኋላ፣ በሉሚዮስ ከተማ (Lumiose City) በስተደቡብ በኩል የሚገኘው ዋይልድ ዞን 1 አጠገብ በሚገኘው የፖኪሞን ምርምር ላብራቶሪ አቅራቢያ ላይ አዲስ የጎንዮሽ ተልዕኮ ካርታዎት ላይ ይመጣልዎታል። እዚህ ነው እንግዲህ የቅሪተ አካል አደናችሁ ሀ ብሎ የሚጀምረው። 

በመቀጠል Revived from a Fossil የተባለውን ተልዕኮ ይቀበሉ እና ወደ ላብራቶሪው ፎቅ ሲወጡ፣ ትልቅ ክብ ቅርጽ ያለው የቅሪተ አካል መመለሻ ማሽን ጎን የቆመ አዲስ ተመራማሪ ያገኛሉ። እሱም መሳሪያው እንዴት እንደሚሰራ ማብራሪያ ይሰጥዎ እና የመጀመሪያውን ቅሪተ አካል መዣ 20,000 ፖኪዶላር ይሰጥዎታል። 

በመቀጠል ከላብራቶሪው በስተሰሜን በኩል የሚገኘው ቬርኔል አቬኑ (Vernale Avenue) ላይ ወደሚገኘው የድንጋይ መሸጫ (Stone Emporium) ይሂዱ። ይህ መደብር ብርቅዬ ድንጋዮች እና ቅሪተ አካላትን የሚያቀርብ ሲሆን፣ ለሽያጭ የቀረቡ ሦስት የተለያዩ ቅሪተ አካላትን ያገኛሉ፡- 

  • Jaw Fossil → የታይራንትን (Tyrunt) ሕይወት ይመልሳል 

  • Fin Fossil → የአማውራን (Amaura) ሕይወት ይመልሳል 

  • Old Amber → ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ኤሮዳክቲልን (Aerodactyl) ጌሙ ላይ ያስከፍታል 

እያንዳንዱ ቅሪተ አካል 20,000 ፖኪዶላር የሚያወጡ በመሆናቸው፣ ሁሉንም የመግዛት እቅድ ካላዎት በቂ ገንዘብ መያዝዎን ያረጋግጡ። ግዢዎትን ከፈጸሙ በኋላ ወደ ምርምር ላብራቶሪው ይመለሱና በድጋሚ ሳይንቲስቱን ያግኙ። እሱም ቅሪተ አካሉን ወደ ነበረበት የሚመልሰው ማሽን ውስጥ ያስገባው፣ እና ከአጭር ቪዲዮ በኋላ የፖኪሞንዎ ሕይወት ይመለሳል። 

በፖክሞን ሌጀንድስ፡ ዜድ-ኤ ውስጥ የሚገኙ የቅሪተ አካል ፖኪሞኖች ሙሉ ዝርዝር እና ኢቮሉሽን ወይም ሜጋ ኢቮሉሽን ሁኔታ፡- 

  • Tyrunt → Tyrantrum፦ ቀን ላይ ብቻ፣ ደረጃ 39 ላይ ይቀየራል። 

  • Amaura → Aurorus፦ ሌሊት ላይ ብቻ፣ ደረጃ 39 ላይ ይቀየራል። 

  • Aerodactyl → Mega Aerodactyl፦ Aerodactylite ሲይዝ ሜጋ ኢቮልቭ ማድረግ የሚችል ሲሆን፣ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ጌሙ ላይ ሊያገኙት ይችላሉ። 

እነዚህ ፖኪሞኖች ልዩ ዓይነትና ቅርጽ አላቸው። ታይራንትረም (Tyrantrum) የሮክ/ድራጎን ዝርያ ሲሆን አስደናቂ ኃይለኛ አካላዊ ጉዳቶችን ማድረስ ይችላል። አውሮረስ (Aurorus) ደግሞ ከባድ የበረዶ እንቅስቃሴዎችን በመጠቀም የድራጎን ዝርያዎችን የሚያጠቃ የሮክ/በረዶ ዝርያ ነው፤ ኤሮዳክቲል (Aerodactyl) ደግሞ በጣም ፈጣን ከሚባሉት የሮክ/ፍላይንግ ፖኪሞኖች አንዱ ሲሆን ጥቃት ለሚያደርሱ ቡድኖች ተመራጭ ነው። 

ሻይኒ (Shiny) አዳኝ ከሆኑ አስደሳቹ ነገር፤ የቅሪተ አካል ፖኪሞኖች ሻይኒ መሆን መቻላቸው ነው። ሆኖም፣ ሻይኒ ቻርም (Shiny Charm) የቅሪተ አካል ፖኪሞኖች ላይ ተጽዕኖ መፍጠር አይችልም፣ እንዲሁም ሻይኒ የመገኘት እድሉ በግምት ከ4,060 ውስጥ 1 ቢሆን ነው። እድልዎን ከፍ ለማድረግ ቅሪተ አካሎችን ወደ ነበሩበት ከመመለስዎ በፊት የጨዋታ ሂደትዎን ሴቭ ያድርጉ። ፖኪሞኑ ከተመለሰ በኋላ ሻይኒ ካልሆነ፣ አስቀምጠዎት የነበረውን ሪሎድ በማድረግ እንደገና ይሞክሩ። ይህ ዘዴ ቅሪተ አካል ፖኪሞኖችን ዳግም ማስጀመር የሚችሉበት ፈጣኑ መንገድ ነው። 

ትዕግስትዎን እና ፖኪዶላርዎን በማቀናጀት ታይራንትረምን፣ አውሩረስን እና ሜጋ ኤሮዳክቲልን በቀላሉ መሰብሰብ ይችላሉ። ቅሪተ አካላትን ወደ ነበሩበት መመለስ ጥሩ ትዝታን ከመቀስቀሱም በተጨማሪ ፖክሞን ሌጀንድስ፡ ዜድ-ኤ ውስጥ ቡድናችሁን ብርቅዬና ኃይለኛ በሆኑ ፖኪሞኖች ማጠናከር የሚችሉበት ምርጥ መንገድ ነው። 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !