icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ፖክሞን ሌጀንድስ፣ ዜድ-ኤ ላይ እስከ 3 የሚደርሱ ሻይኒ ስቶኖችን እንዴት በነፃ ማግኘት ይቻላል? 

ፖክሞን ሌጀንድስ፣ ዜድ-ኤ ላይ ሻይኒ ስቶን ለማግኘት ቀላሉ መንገድ በሉሚዮስ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የከበሩ ድንጋይ መሸጫ መደበር ከሆነው Jewel of Kalos መግዛት ሲሆን፣ የከተማው እምብርት በሆነው ፍሎሪያል ጎዳና ላይ ከሚገኘው የፖክሞን ማዕከል አጠገብ ያገኙታል። ጌሙ ውስጥ የተወሰነ ያህል ከገፉ በኋላ መደብሩ ውስጥ አንድ ሻጭ የተለያዩ የከበሩ ድንጋዮችን ይሸጥልዎታል። 

ሻይኒ ስቶን ጌሙ ሲጀምር ጀምሮ የሚገኝ አይደለም። መደብሩ ውስጥ ለማስክፈት የታሪኩን ዋና ተልዕኮ 39 ማጠናቀቅ አለብዎት። ይህን ተልዕኮ ካጠናቀቁ በኋላ ብቻ 3,000 ፖክዶላር በማውጣት መግዛት ይችላሉ። በተለይም ከተማው ውስጥ ያለውን እያንዳንዱን ጥጋ ጥግ በመፈተሽ ሰዓታትን ማጥፋት ሳይጠበቅብዎ በርካታ Grass- or Fairy-type Pokémon ማሻሻል ሚፈልጉ ከሆነ ዋጋው ተመጣጣኝ በመሆኑ ቢገዙት ይመከራል። 

Jewel of Kalos በእድል ብቻ መተማመን ለማይፈልጉ ተጫዋቾች በጣም አስተማማኝ አማራጭ ሲሆን፣ አንዴ ከተከፈተ በኋላም ያለ ምንም ገደብ የሚፈልጉትን ያህል ሻይኒ ስቶን መግዛት ያስችልዎታል። እንዲሁም ፖክዴክስዎን ለማጠናቀቅ ወይም የተለያዩ የቡድን ግንባታዎችን ለመሞከር እየሞከሩ ከሆነ ፍጹም ተመራጭ ነው። 

አይይ! እኔ በነፃ ነው ማግኘት የምፈልገው ካሉ፣ ሉሚዮስ ከተማን በማሰስ በነፃ ማግኘት የሚችሉባቸው የተወሰኑ አማራጮች አሉ። ከጨዋታው ጅማሮ አንስቶ ከተማዋ ብርቅዬ እቃዎችን እና ሻይኒ ስቶኖችን በያዙ Poke Balls የተሞሉ ድበቅ ቦታዎች የተሞላች ከተማ ነች። እነዚህን ብርቅዬ እቃዎች ማግኘት የሚችሉባቸው ሦስት ታዋቂ ቦታዎች ቀጥለን አዘጋጅተንልዎታል፦ 

ቦታ 1፦ 

የመጀመሪያው ሻይኒ ስቶን በከተማው ምዕራባዊ ክፍል በሚገኝ ትንሽ ግቢ ውስጥ ተደብቆ ይገኛል። ወደ ቦታው ለመሄድ ወደ መገበያያ አካባቢው ይሂዱ እና ትልቁ ፏፏቴ ጋር ሳይደርሱ በፊት ወደ ግራ ሲታጠፉ፣ ከብረት የተሰራ ቆሻሻ መጣያው ጀርባ የተቀመጠ Poke Ball ያገኛሉ። ኳሱን በመውሰድ የመጀመሪያውን ሻይኒ ስቶን ማግኘት ይችላሉ። 

 

ቦታ 2፦ 

ሌላኛው ሻይኒ ስቶን የህንፃ ግንባታ መወጣጫ ላይ ይገኛል። ወደ ላይ ይውጡ እና ተቃራኒው መወጣጫ ላይ ለመድረስ የY ቁልፍን በመጫን ሲንከባለሉ፣ ሻይኒ ስቶን የያዘ Poke Ball ያገኛሉ። ይህ ቦታ ትንሽ ጊዜ አጠባበቅን ይጠይቃል፣ ነገር ግን ሉሚዮስ ውስጥ የተለያዩ የእንቅስቃሴ መካኒክሶችን መለማመድ ያስችልዎታል። 

ቦታ 3፦ 

በመጨረሻም ከሊሳንድሬ ፓርክ አጠገብ የሚገኘው ሕንፃ ላይ ሲሆን መሰላሉን በመጠቀም ጣሪያው ላይ ይውጡ። አንደኛው ላይ ሻይኒ ስቶን የያዘ ሌላ Poke Ball ያገኛሉ። ይህ አካባቢ ትንሽ ድበቅ ቢሆንም፣ ከተማዋን ከጫፍ እስከ ጫፍ በግልጽ መጎብኘት እና በዙሪያው የሚገኙ ተጨማሪ ግርሻዎችን ማሰስ ተገቢ ነው። 

እነዚህን ሶስት ቦታዎች በመጠቀም እስከ ሶስት ሻይኒ ስቶኖችን ገና ከጅማሮዎ በቀላሉ መሰብሰብ ይችላሉ። ይህም ብርቅዬ እቃዎችን እየሰበሰቡ ፖክዶላሮዎን መቆጠብ ያስችልዎታል። ሮዜሊያን ወደ ሮሴራዴ ወይም ፍሎትን ወደ ፍሎርጅስ ለመቀየር እያሰቡ ከሆነም፣ እነዚህ ድንጋዮች በፖክሞን ሌጀንድስ፣ ዜድ-ኤ ውስጥ ቡድናቸውን ማጠናከር ለሚፈልጉ አሰልጣኞች ወሳኝ ጥቅም ይሰጣሉ።  

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !