icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ARC Raiders ውስጥ Seeker ቦምቦችን እንዴት ማግኘት እና መጠቀም
ይቻላል?

ARC Raiders ውስጥ Seeker Grenades ወይም አሳዳጅ ቦምቦች በመባል የሚታወቁት የቦምብ ዓይነቶች
ጌሙ ውስጥ ካሉ እጅግ ጠቃሚ እና ኃይለኛ መሣሪያዎች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው። እነዚህ ቦምቦች ራስዎን
ለአደጋ ሳያጋልጡ ጠላትን ለማስጨነቅ፣ ከመሸገበት ቦታ እግሬ አውጪኝ ብሎ ለማስፈርጠጥ ወይም ደግሞ
አቅጣጫውን ለማስቀየስ የሚያስችሉ ድንቅ መሣሪያዎች ናቸው። ይሁንና እነዚህ ቦምቦች ገና ጌሙን እንደጀመሩ
እንደማንኛውም ተራ ዕቃ ሜዳ ላይ ተጥለው የሚያገኟቸው አይደሉም።


እነዚህን ቦምቦች ለማስከፈት የተወሰነ ብዛት ያላቸው የልምድ ነጥቦች (XP milestones) አስፈላጊ በመሆናቸው
በቅድሚያ የአካውንትዎን ደረጃ ማሳደግ ይኖርብዎታል። ስለዚህ የሚጠበቅብዎ ደረጃ ላይ እስካልደረሱ ድረስ በዕቃ
መያዣዎ (inventory) ወይም በሎድ አውት (loadout) ዝርዝርዎ ውስጥ አያገኟቸውም። ይህንንም ለማድረግ
ተከታታይ ግጥሚያዎች ላይ መሳተፍ፣ የጎንዮሽ ተልዕኮዎችን መወጣት፣ እንዲሁም ከሁሉም በላይ ደግሞ ከአደገኛ
ሁኔታዎች በሕይወት መውጣት ወሳኝነት አለው፤ ይህ የሆነውም ያከማቹት XP በቋሚነት የሚመዘገበው
በሕይወት መትረፍ ከቻሉ ብቻ በመሆኑ ነው።


አንዴ አስፈላጊው የXP ደረጃ ላይ እንደደረሱ Seeker ቦምብ፣ የሎድ አውት ዝርዝራችሁ ክፍል ውስጥ የሚገኘው
የቦምብ/ የመገልገያዎች ዝርዝር ስር ያገኙታል። እዚህ ጋር ግን ማወቅ ያለብዎ ነገር አለ፤ ቦምቡ ስለተከፈተ ብቻ
በቀጥታ መደበኛ ቦምቦችዎን ይተካል ማለት አይደለም። ስለዚህ ተልዕኮ ከመጀመርዎ በፊት ቀድመው መታጠቅ
ይኖርብዎታል። በርካታ ተጫዋቾች መሣሪያው ተከፍቶልናል ብለው በመዘናጋት ሳይታጠቁ ስለሚገቡ ሜዳ ላይ
ብዙ ጊዜ ሲቸገሩ ይስተዋላሉ።


በውጊያ ወቅት አጠቃቀማቸው ቀላል ቢመስልም፣ የሚያደርሱት ጉዳት ግን እጅግ ከፍተኛ ነው። ቦምቡን አንዴ
ከወረወሩት በኋላ በአካባቢው ያለን ጠላት (ተጫዋችም ይሁን ARC) ዱካ በማነፍነፍ ይከተላቸዋል። ከጥቅሞቹም
መካከል፦ አደገኛ ቦታዎችን ለመቃኘት ወይም ሕንጻ ውስጥ ጠላቶች መኖራቸውን ለማረጋገጥ፣ ተደብቆ
የሚያስጨንቅ ጠላትን ከመሸገበት ቦታ አስገድዶ ለማስወጣት፣ በተናጠል ለሚጫወቱ ተጫዋቾች ያለምንም ስጋት
መረጃ እንዲያገኙ፤ እንዲሁም ለቡድን ተጫዋቾች የተቀናጀ ጥቃት ከመሰንዘራቸው በፊት እንደ መቀስቀሻ ወይም
ማስጀመሪያነት ያገለግላል።


የእነዚህን ቦምቦች ከፍተኛ አቅም ለመጠቀም የሚጠቀሙትን አወቃቀር (build) ማስተካከል ይመከራል። የተወሰኑ
ፐርኮች (perks) እና ሞጁሎች በበኩላቸው የቦምቡን ድግግሞሽ፣ የሚሸፍነውን ርቀት እና አጠቃላይ የጥቃት
አቅሙን ይጨምራሉ። በተጨማሪም፣ ሙሉ በሙሉ min-max ሂደት ውስጥ መግባት ሳይጠበቅብዎ፤ የቦምቡን
ድጋሚ የመሰናጃ ጊዜ (cooldown) መቀነስ ወይም የመገልገያዎችዎን ብዛት መጨመር ረጅም ቆይታ ያላቸው
ውጊያዎች ላይ አስደናቂ ልዩነት ይፈጥርልዎታል።


መልካም ጨዋታ

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !