
ARC Raiders ውስጥ እጅግ ተፈላጊ የሆነውን የAphelion መሣሪያ ንድፍ ለማግኘት ሁለት መንገዶች አሉ።
የመጀመሪያው ንድፉን ማግኛ እጅግ አስተማማኝ መንገድ Matriarch የተባለችውን ግዙፍ ቦስ ማሸለፍ ነው።
ይህች ቦስ እንደ Stella Montis ባሉ ማፖች ላይ በሚደረጉ የBlue Gate ዝግጅቶች ወቅት የምትገኝ ሲሆን፣
ይህችን ቦስ አንዴ ድል ከነሷት በኋላ የAphelion ንድፍን የያዘ ሣጥን ትጥላለች። እዚህ ጋር ግን ማወቅ ያለብዎ
ነገር፣ ኮንቴይነሩን መውሰድ የሚችለው አንድ ተጫዋች ብቻ በመሆኑ፣ ውጊያው ሲያልቅ ከሌሎች ሬደሮች ጋር
ከፍተኛ ሽሚያ ውስጥ መግባትዎ አይቀሬ ነው።
በቡድን የሚጫወቱ ከሆነ ትኩረታችሁን የቦሷ ደካማ የመገጣጠሚያ ክፍሎች እና ልቧ ላይ በማድረግ Anti-armor
መሣሪያዎችን መጠቀም ይመከራል። በተናጠል የሚጫወቱ ከሆነ ደግሞ፣ ቦሷ የምትሰነዝራቸውን ጠንካራ ጥቃቶች
(AoE) ለመከላከል ወጥመዶችን መጠቀም፣ ያለማቋረጥ መንቀሳቀስ እና በንቃት መከታተል ወሳኝነት አለው።
አስደሳቹ ዜና፣ ከፓች (patch) 1.7.0 ወዲህ የንድፉ የመገኘት ዕድል በመጨመሩ፣ ተጫዋቾች በተደጋጋሚ
መሰብሰብ እንዲችሉ አመቺ አድርጎታል።
የዝግጅቶች ጥገኛ መሆን ካልፈለጉ ደግሞ፣ Stella Montis ማፕ ላይ በሚገኙ የተቆለፉ ክፍሎች ውስጥ ንድፉን
ማግኘት ይችላሉ። ከእነዚህም መካከል በስተምዕራብ በኩል የሚገኘው የሕክምና ጥናት ጣቢያ ዋነኛ የሚያገኙበት
ቦታ ነው። ይህ ቦታ በPops፣ Bolides እና Shredders የተሞላ አደገኛ የሚባል ቀጠና ነው። ሆኖም ወደዚህ
ቀጠና ከመግባትዎ በፊት የStella Montis የሕክምና መጋዘን ቁልፍን ማግኘት ይኖርብዎታል። ቁልፉንም
በአቅራቢያው ባሉ ሕንጻዎች ውስጥ የሚገኙ የቆሻሻ ማጠራቀሚያዎችን፣ ጠረጴዛዎችን ወይም ካቢኔቶችን
አብጠርጥሮ በመፈተሽ ማግኘት ይችላሉ።
አንዴ ቁልፉን ካገኙ በኋላ ወደ ህንጻው የመጀመሪያ ፎቅ በመግባት የሚያገኟቸውን ሣጥኖች፣ መሳቢያዎች እና
ካቢኔቶች ሁሉ በመዝረፍ ወዲያው የሰበሰቧቸውን ንብረቶች ይዘው በፍጥነት ከአካባቢው ይሰወሩ። ቦታው የPvP
ፍጥጫ የሚበዛበት በመሆኑ ድምፅ ሳያሰሙ መንቀሳቀስ እጅግ አስፈላጊ ነው። የደፈጣ ወይም ድንገተኛ ጥቃቶችን
ለመከላከልም የጭስ ቦምቦችን እና ድምፅ አልባ መሣሪያዎችን መጠቀም ወሳኝነት አለው።
ንድፉን አንዴ እጅዎ ውስጥ ካስገቡ በኋላ፣ ወደ ደረጃ 3 መሣሪያ ሠሪ ጋር በመውሰድ መሣሪያውን ማሰራት
ይችላሉ። ይህን ለማድረግም 1 Matriarch Reactor፣ 3 Magnetic Accelerators፣ 3 Complex Weapon
Parts ግብዓቶች ያስፈልጉዎታል። እነዚህ ግብዓቶች በቀላሉ የሚገኙ አይደሉም፤ አብዛኛውን ጊዜ በLegendary
ሣጥኖች ውስጥ ወይም ትልልቅ ቦሶች በሚጣሏቸው ዕቃዎች ውስጥ የሚገኙ ናቸው። ስለዚህ Stella Montis እና
የARC ዝግጅቶች እነዚህን ግብዓቶች ማግኘት የሚችሉባቸው ምርጥ መንገዶች ናቸው።
መልካም ጨዋታ