
በEA Sports FC 26 Ultimate Team ውስጥ፣ የተወሰኑ የታክቲክ እና የአጨዋወት ዘይቤዎች አስደናቂ
ውጤቶችን እያስገኙ ይገኛሉ። እነዚህን ስልቶች በሚገባ መረዳት የተጋጣሚን እንቅስቃሴ ቀድማችሁ ለመገመት፣
የቡድን ስብጥራችሁን ለማስተካከል እና በርካታ ጨዋታዎችን ማሸነፍ ያስችላችኋል።
የመጀመሪያው እና ከፍተኛ ጫና መፍጠር የሚያስችለው 4-3-3 (Intense Pressing) አሰላለፍ ሲሆን ይህ
አሰላለፍ በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ደረጃ በተጫዋቾች ዘንድ የሚዘወተር ሲሆን፣ Press After Possession Loss
(PAPL) እና ወደ ተከላካይ መስመር ማስጠጋት (High Line) ላይ የተመሠረተ ታክቲክ ነው። ይህም ኳስን
በፍጥነት ለመቀማት እና ተቃራኒ ቡድን ላይ ተከታታይ ጫናን በመፍጠር በርካታ ጎል የማስቆጠር ዕድሎችን
መፍጠር ያስችላል። መልሶ ለማጥቃትም ወደ ክንፍ ተጫዋቾቻችሁ ወይም ወደ ፊት መስመር አጥቂዎቻችሁ
ረጅም ኳሶችን በማሻማት የተጋጣሚን ጫና መስበር እና የሚፈጥሯቸውን ክፍት ቦታዎች ጥቅም ላይ ማዋል
ትችላላችሁ።
ሁለተኛው 4-2-3-1 (Slow Possession) ሲሆን፣ ይህ አጨዋወት የጨዋታውን ፍጥነት በመቀነስ፣ ኳስን
በቁጥጥር ስር ማዋል እና ተቃራኒው ቡድን ተዘናግቶ ክፍተት እስኪፈጥር በትዕግሥት መጠበቅ ላይ ያተኮረ ነው።
ይህን ለማክሸፍም የተቃራኒ ቡድን አጥቂ አማካዮች ላይ ያነጣጠረ ጫና መፍጠር አለባችሁ። በሜዳው መካከለኛ
ክፍል ላይ የሚደረግ የTrap Press ጨዋታም የአጨዋወት ፍሰታቸውን በማስተጓጎል ኳሱን ለመቀማት
ይረዳችኋል።
ለልዩ ታክቲክ ደግሞ የLow Width + Short Passing + lure press ጥምር ቀጥተኛ አጨዋወትን ለሚከተሉ
ቡድኖች እራስ ምታት የሆነ ስልት ነው። ቡድናችሁ በመካከለኛ ክፍል ላይ ተቀራርበው እንዲቆሙ በማድረግ
ክፍተቶችን መዝጋት የሚያስችል ሲሆን፤ በተጨማሪም ተቃራኒው ቡድን በክንፍ በኩል ብቻ እንዲጫወት
ያስገድዳል። ይህን ስልት ለማክሸፍ ሰፊ ቦታ ለመሸፈን እና ጨዋታችሁን በክንፍ በኩል ለመቀየር ሞክሩ። ይህም
ተቃራኒው ቡድን መኃል ላይ ብቻ አተኩሮ ስለሚከላከል፣ ጨዋታውን ወደ ክንፍ በማስፋት ለመስቀለኛ ኳሶች
(Crossing) የሚመቹ ቦታዎችን መፍጠር ያስችላችኋል።
መከላከልን በተመለከተ፣ ብዙ ተጫዋቾች ጫናን ተቋቁመው ፈጣን የመልሶ ጥቃቶችን (Counter-attack)
ለመሰንዘር "Drop Back" እና Conservative Interceptionsን ይጠቀማሉ። ስለዚህ ኳሱን በቁጥጥራችሁ ስር
አውላችሁ ወደ ተቃራኒው ቡድን በማዞር፤ ከተከላካዮች ጀርባ በኩል አግድም ኳሶችን (Diagonal passes)
በመጠቀም ተጫወቱ። ይህ አጨዋወት ተከላካዮቹ ቦታቸውን ዳግም ለማስተካከል በሚሞክሩበት ወቅት ጥቃት
ለመሰንዘር ክፍተት ይፈጥራላችኋል።
ፈጣን እና ገፍተው የሚመጡ መልሶ የማጥቃት ስልቶች ድንገተኛ ሊሆኑባችሁ ቢችሉም፣ ተቃራኒው ቡድን
ለመከላከል በሚመለሱበት ወቅት (Defensive transition) ሰፊ ክፍተቶችን ይፈጥራሉ። ይህ ሲሆንም
አማካዮቻችሁ ወደ ፊት በመሄድ (Overlap) ከፊት መስመር አጥቂዎች ጋር እንዲጣመሩ አድርጉ። ይህም
ተቃራኒው ቡድን በሙሉ ኃይሉ ጥቃት ሰንዝሮ ሲመለስ፣ ከኋላ የተወውን ክፍት ቦታ መጠቀም ያስችላችኋል