icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

የFortnite እና South Park አልባሳት፣ መሸጫ ዋጋ እና ተጨማሪ ዝርዝር
መረጃዎች

 

ፎርትናይት ከጥቂት ተጫዋቾች በስተቀር ማንም ያልገመተውን አዲስ ሽርክና ይዞ በመቅረብ በድጋሚ ድፍን
ዓለምን አስደምሟል። ሙሉ በሙሉ በአስደናቂ ነገሮች የተሞላው የSouth Park ዓለም በይፋ ፎርትናይትን
የተቀላቀለ ሲሆን፣ ይህ ዝግጅት ቅምሻዎችን ሳይሆን የተንበሸበሸ ተሞክሮን የሚሰጡ አስደናቂ ነገሮችን አሟልቶ
ነው የመጣው። ይህ ዝግጅት ለአንድ ወር ያህል የፎትርናይት ደሴትን የሚያናውጡ አልባሳትን፣ ልዩ ልዩ ቁሳቁሶችን፣
አዳዲስ ቦታዎችን እና አዳዲስ የጨዋታ ስልቶችን አካቷል።


ይህ ሽርክና ከJanuary 9 እስከ February 5፣ 2026 ድረስ የሚቆይ ሲሆን፣ በእነዚህ ጊዜያት በBattle Royale
እና Zero Build ሞዶች ውስጥ ልዩ ይዘቶችን ማግኘት ይቻላል። የEpic Games ግብ ጥቂት አልባሳትን መደብሩ
ውስጥ መደርደር ብቻ ሳይሆን፣ የSouth Parkን ለየት ያሉ ሆድ የሚያቆስሉ ኩምክናዎችን እና ጅብዶችን
ከፎርትናይት ጋር ሙሉ በሙሉ ማዋሃድን ያለመ ነው።


ወደ አልባሳቱ ስንመጣ፣ የተከታታይ ፊልሙ ታዋቂ ገፀ-ባሕሪያት የሆኑት Cartman፣ Stan፣ Kyle፣ Kenny እና
Butters የፎርትናይትን ዘይቤ ባማከለ መልኩ ዝርዝሩ ውስጥ የተካተቱ ሲሆን ከmech አልባስ እና ከጋሻ ጋር ለገበያ
ቀርበዋል። የአንድ አልባስ መሸጫ ዋጋ 1,500 V-Bucks ሲሆን፣ ይህም እንዲህ ባሉ አንጋፋ ሽርክናዎች ላይ
የተለመደ ዋጋ ነው። ሁሉንም በአንድ ላይ ለመግዛት ለሚፈልጉ ተጫዋቾች ደግሞ ከ4,000 V-Bucks በታች በሆነ
ዋጋ ጥቅሉን መግዛት ይችላሉ፤ ይህም ጥቅል እያንዳንዱን ለየብቻ በመግዛት የሚወጣ ወጪን የሚቀርፍ አዋጭ
አማራጭ ነው። በተጨማሪም የተከታታይ ፊልሙ ቀንደኛ አፍቃሪያን ለሆኑ ተጫዋቾች ታውሊ ለብቻው ለሽያጭ
ቀርቧል።


ሽርክናው በዚህ ብቻ አያበቃም። ማፑ ላይ የSouth Parkን ትርክቶች የሚዳሰስ ልዩ ቦታ የተጨመረ ሲሆን፣
አንዳንድ ጊዜያዊ ቁሳቁሶች ደግሞ የጨዋታውን ሕግ ወይም የአውሎ ነፋሱን አካሄድን እስከመቀየር ይደርሳሉ።
ከዚህም ባለፈም ፎርትናይት ተጫዋችች ምንም ወጪ ሳያወጡ ልዩ ልዩ ሽልማቶችን እና አልባሳትን የሚያስገኙ
ተልዕኮዎችን የያዘ ነፃ mini-pass አዘጋጅቷል።


መልካም ጨዋታ

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !